ዜናፖለቲካ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና፡ አልሸባብ በሶማሌ ክልል ሊፈጽመው አቅዶት የነበረው የአጥፍቶ መጥፋት ጥቃት መክሸፉን መከላከያ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22/2016 .ም፡ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአሸባሪነት የተፈረጀው አልሸባብ በሱማሌ ክልል በዶሎ አዶ ወረዳ ሊፈጽመው የነበረው የሽብር ጥቃት መክሸፉን የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ብይፋዊ የፌስቡክ ገጹ ባወጣው መረጃ አስታወቀ።

የሽብር ቡድኑ ወደ ወረዳው ዘልቆ በመግባት ስድስት ጀሪካን ተቀጣጣይ ኬሚካል 3000 የብሬን ጥይት በመያዝ በአጥፍቶ ጠፊዎች ጥቃት ሊፈፅም አቅዶ እንደነበር የጠቆመው መረጃው በመከላከያ ሠራዊት እና በዶሎ አዶ ወረዳ የፀጥታ አካላት በቁጥጥር ስር መዋሉን ገልጿል።

የሽብር ቡድኑ ከዚህ ቀደምም በሀገር ላይ ውድመት እና ሽብር ለማድረስ ተደጋጋሚ ሙከራዎችን ያደረገ መሆኑን ብረጋዴር ጀነራል ጌታቸው ሀብታሙ ከሥፍራው እንደገለፁለት ያስታወቀው የመከላከያ ሰራዊቱ መረጃ ነገር ግን በሠራዊቱና በህዝቡ የነቃ ክትትል የሽብር ቡድኑ ሃሳብ ሳይሳካ በቁጥጥር ስር እየዋለ ይገኛል ማለታቸውን አመላክቷል።

በተጨማሪም በአከባቢው የሰፈረው የመከላከያ ሀይሉ አመራር የሆኑት መቶ አለቃ ፈንታ አየለ በበኩላቸው በቀጠናው የሚገኘውን የአልሸባብ ቡድን ሆነ የውስጥ እና የውጭ ፀረ ሠላም ሀይሎችን በመመከት ደረጃ የሠራዊቱ ሞራልና ብቃት የላቀ ነው ሲሉ መናገራቸውን አካቷል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button