ዜናፖለቲካ

ዜና፡ ከአፍሪካ ህብረት ስብሰባ በኋላ በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መካከል የተፈጠረው ውጥረት አለመርገቡ እና የሚታይ ለውጥ አለመከሰቱ አሳዛኝ ነው – ተመድ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 11/2016 ዓ.ም፡- በሶማሊያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ ልዩ መልዕክተኛ እና የተመድ የሶማሊያ ተልዕኮ ረዳት ካተሪዮና ሌይንግ ለምክር ቤቱ አባላት ባደረጉት ገለጻ ከአፍሪካ ህብረት ስብሰባ በኋላ በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መካከል የተፈጠረው ውጥረት አለመርገቡ እና የሚታይ ለውጥ አለመከሰቱ አሳዛኝ ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያን እና የሶማሊላንድን የመግባቢያ ሰነድን በተመለከተ የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሸክ መሃሙድ የሚሰጡት አስተያየት የተቆጠበ ቢሆን ይበረታታል ሲሉ ልዩ መልዕክተኛዋ አሳስበዋል።

አልሸባብ ሁኔታውን አዳዲስ ምልምሎችን ለማግኘት እየተጠቀመበትመሆኑ አሳሳቢ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ትላንት የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ መካከል በተፈጠረው ውጥረት ዙሪያ ተወያይቷል። የምክር ቤቱ አባላት በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ መካከል የተፈጠረው አለመግባባት እንዳሳሰባቸው እና ሁለቱ አገራት ጉዳዩን በውይይት እንዲፈቱት ጥሪ አቅርበዋል።

በምክር ቤቱ ተገኝተው የመንግስታቸውን አቋም ያሰሙት በጸጥታው ምክር ቤት የሶማሊያ አምባሳደር የኢትዮጵያ መንግስት የባህር በር ለማግኘት ሲል ከሶማሊላንድ ጋር የፈጸመው ስምምነት ቀጠናውን ብቻ ሳይሆን አለምአቀፍ ቅቡል የሆነውን የነጻ ሀገራት ሉአላዊነትን እና ነጻነትን የሚጻረር ነው ሲሉ ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ በሶማሊያ ምድር ላይ የጦር ሰፈር የምትመሰርት ከሆነ በግልጽ በሶማሊያ እና በህዝቧ ላይ ጦርነት እንዳወጀች የሚቆጠር ነው ብለዋል። የአዲትዮጵያ ተግባር በአልሸባብ ላይ በሶስት አስርት አመታት ጥረት ያገኘነውን ስኬት በመቀልበስ ለሚያደርገው ጥረት አጋዥ ይሆነዋል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

የዚህ አይነት ተግባር ውጤት ውስብስበ የብሔሮች ስብስብ በሆነችው ኢትዮጵያ ላይ አለመረጋጋት ሊያስከትል ይችላል ሲሉ ገልጸዋል። በቀጠናው የሚንቀሳቀሱ የመገንጠል ሀሳብ የሚያቀነቅኑ የብሔር ቡድኖች እንዲያብቡ ምቹ ሁኔታን የሚፈጥር ነው ብለዋል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button