ዜናፖለቲካ

ዜና፡ የሶማሊያ ተግባር የአንዳንድ መገናኛ ብዙሃንን ትኩረት ለመሳብ ያለመ ነው ሲል መንግስት አጣጣለ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 11/2016 ዓ.ም፡- በአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመታደም አዲስ አበባ ከደረሱ በኋላ አቋርጠው ወደ ሀገራቸው የተመለሱትን የሶማሊያ ፕሬዝዳንት አስመልክቶ የሞቃዲሾ መንግስት ያወጣው ውንጀል ከአንዳንድ መገናኛ ብዙሃን ትኩረት ለማግኘት ያለመ ብቻ ነው ሲል የኢትዮጵያ መንግስት አጣጣለ።

የጉባኤውን መጠናቀቅ አስመልክተው የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታዋ ሰላማዊት ካሳ በሰጡት መግለጫ ኢትዮጵያ ለእንግዶቿ ያደረገችውን አቀባበልም ኾነ እንክብካቤ የማይመጥን ነው ሲሉ የሶማሊያን ተግባር ተችተዋል።

ሚኒስትር ዴኤታዋ መግለጫው የሰጡት ላለፉት ሁለት ቀናት በአዲስ አበባ ሲካሄድ የቆየው 37ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ ዛሬ የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም ማለዳ በተካሄደ የመዝጊያ ሥነ-ሥርአት ከመጠናቀቁ አስቀድሞ ነው።

የሶማሊያው ፕሬዝደን ሀሰን ሸክ ማሃሙድ የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤን ለመታደም በአዲስ አበባ ከተገኙ በኋላ የኢትዮጵያ የጸጥታ ሀይሎች ወደ ህብረቱ አዳራሽ ለመታደም ሳደርገው የነበረውን ጉዞ አስተጓጉለውብኛል በሚል አቋርጠው መመለሳቸው ይታወሳል። ፕሬዝዳንት ሀሰን ወደ ሞቃዲኞ ከተመለሱ በኋላ ጽ/ቤታቸው በሰጠው መግለጫ የኢትዮጵያ የጸጥታ ሀይሎች ወደ ስብሰባው እንዳላመራ በሆቴል ላይ እያለሁ አደናቅፈውኛል የሚል ምክንያት አቅርበዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባዩ አምባሳደር መለስ አለም የሶማሊያን መግለጫ ተቀባይነት የሌለው ሀሰት ነው ሲሉ ትላንት ማስተባበላቸው ይታወሳል።

የኅብረቱ አባል ሀገራት መሪዎች የደኅህንነት ስጋት እንዳይገጥማቸው ኢትዮጵያ ሙሉ ኀላፊነቱን ወስዳ ስለመሥራቷም ሚኒስትር ዴኤታዋ በመግለጫቸው አመላክተዋል።

ባለፉት ስድስት ወራት የኀብረቱ ጉባኤ ስኬታማ እንዲኾን ሀገሪቷ ትኩረት ሰጥታ ከተለያዩ ተቋማት ጋር ዝግጅት ስታደርግ መቆየቷን ገልጸዋል፡፡ በብዙ መስፈርትም ሀገሪቱ ጥቅሞቿን በሚያረጋግጥ መንገድ ጉባኤውን አስተናግዳ ማጠናቀቋን ነው ሚኒስትር ዴኤታዋ ያብራሩት፡፡

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

በሌላ ዜና በአዲስ አበባ በአፍሪካ የመሪዎች ስብሰባ ላይ የታደሙት የብራዚሉ ፕሬዝዳንት ሉላ ዳ ሲልቫ በጎባኤ ላይ ባደረጉትን ንግግር እስራኤል በጋዛ እያካሄደች ያለውን ዘመቻ በአይሁዳውያን ላይ ከተፈጸመው የጅምላ ፍጅት ጋር በማነጻጸር የዘር ማጥፋት ነው ማለታቸውን እስራኤልን እንዳስቆጣ እና ማውገዟን የተመለከቱ በርካታ ዘገባዎች ተስተናግደዋል።

ፕሬዝዳንት ሉላ የእስራኤልን ወታደራዊ እርምጃ “በከፍተኛ ደረጃ በተዘጋጀ ሠራዊት እና በሴቶች እንዲሁም በህጻናት” መካከል የሚካሄድ ነው ብለዋል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button