ዜናፖለቲካ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና፡ የአፍሪካ ልማት ባንክ በሁለት የአዲስ አበባ ሰራተኞቼ ላይ እስር እና ድብደባ ተፈጽሟል፣ ይህም ከፍተኛ የዲፕሎማቲክ መብት ጥሰት ነው ሲል ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 6/2016 ዓ.ም፡- የአፍሪካ ልማት ባንክ በአዲስ አበባ በሚገኘው ቢሮው ባልደረባ የሆኑ ሁለት ሰራተኞቹ ላይ የኢትዮጵያ የጸጥታ ሀይሎች ከህግ አግባብ ውጭ አስረዋቸው እንደነበር፣ ድብደባ እንደፈጸሙባቸው እና የዲፕሎማቲክ መብት ጥሰት እንደደረሱባቸው አስታወቀ።

ከሳምንታት በፊት በሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን የአፍሪካ ልማት ባንክ ከፍተኛ ሃላፊዎች ድብደባ እንደተፈጸመባቸው እና ለእስር መዳረጋቸውን የተመለከቱ ዘገባዎች ተሰራጭተዋል።

ባንኩ ለአዲስ ስታንዳርድ በላከው ደብዳቤ እንደገለጸው የተፈጸመባቸው እስር ከፍተኛ የዲፕሎማቲክ መብት ጥሰት ነው ሲል ተችቶ ስለሁኔታው ለኢትዮጵያ መንግስት ማስታወቁን እና ተቀባይነት ማግኘቱን፣ ነገር ግን ስለ ተፈጸመባቸው ድብደባም ሆነ ስለ አመራሮቹ ማንነት አልገለጸም።

እንደ የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘገባ ከሆነ ድብደባ ከተፈጸመባቸው የባንኩ ከፍተኛ አመራሮች መካከል ዶ/ር አብዱል ካማራ የልማት ባንኩ የምስራቅ አፍሪካ ምክትል ዳይሬክተር እና የኢትዮጵያ የባንኩ ማናጀር መሆናቸው ተጠቁሟል።

መገናኛ ብዙሃኑ በተጨማሪ ባንኩ የኢትዮጵያ ቢሮውን መዝጋቱን እና ስራ ማቆሙን አስታውቀዋል። አዲስ ስታንዳርድ ለባንኩ በተደጋጋሚ በኢሜይል ጉዳት የደረሰባቸውን ሰራተኞቹን ማንነት ለማወቅ ያደረገችው ጥረት ምላሽ ሳያገኝ ቆይቷል። ባንኩ ስለ ሁኔታው እና ስለማንነታቸው ሊያረጋግጥልንም ሆነ ሊያምን አልቻለም።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሳምንታዊው ጋዜጣው መግለጫው ላይ ከሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ጋዜጠኞች የግጭቱ መነሻ በባንኩ እና በገንዘብ ሚኒስቴር መካከል ኢትዮጵያ ለባንኩ መከፍል የሚጠበቅባትን አመታዊ ክፍያ ካለመክፈሏ ጋር በተያያዘ እንደሆነ እና በዚህም ሳቢያ ባንኩ የአዲስ አበባ ቢሮውን ለመዝጋት መወሰኑ እውነት መሆኑን በተመለከተ የተጠየቁት ቃል አቀባዩ አምባሳደር መለስ አለም የተፈጠረው ሁኔታ የባንኩን እና የመንግስትን ግንኙነት አልጎዳውም ባንኩም ቢሮውን አልዘገባ ሲል ምልሻ መስጠታቸው ተዘግቧል።

የአፍሪካ ልማት ባንክ በይፋዊ መግለጫው ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ስለሁኔታው እንደሰሙ ወዲያውኑ ጉዳት የደረሰባቸው እና ለእስር የተዳረጉት የባንኩ ከፍተኛ አመራሮች እንዲለቀቁ ትእዛዝ ማስተላለፋቸውን እና ሁኔታውን በተመለከተ ገለልተኛ ምርመራ እንደሚደረግ ቃል መግባታቸውን ጠቅሶ አወድሷል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

በተጨማሪም ባንኩ ለአጋሮቹ ባስተላለፈው መልዕክት ሁኔታው በኢትዮጵያ በሚያከናውነው ስራው ላይ ተጽእኖ እንደማያሳድር ለማረጋገጥ እንወዳለን ብሏል።

ባንኩ ለኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ስለሁኔታው ግልጽ ቅራኔውን ማቅረቡን ያስታወቀው መግለጫው ሁኔታው ከፍተኛ የዲፕሎማቲክ መብት ጥሰት ነው ሲል ኮንኗል።

የኢትዮጵያ መንግስት የባንኩን ቅሬታ ሙሉ በሙሉ እንደተቀበለ ባይገልጽም ድርጊቱ መፈጸም ያልነበረበት መሆኑን ግን እንደሚቀበል፣ የህግ ጥሰቱን የፈጸሙትን ለመለየት ምርመራ እንደሚያካሂድ እና ለፍርድ እንደሚያቀረብ፣ ግልጽነት እና ተጠያቂነት እንደሚያሰፍን አረጋግጦልኛል ሲል ባንኩ በመግለጫው አመላክቷል።

የባንኩ የኢትዮጵያ ሰራተኞችም ሆኑ ለተልዕኮ ወደ ሀገሪቱ የሚገቡ ባልደረቦቻቸው በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ የዲፕሎማሲ ሙሉ መብታቸው እንደሚጠበቅላቸው የኢትዮጵያ መንግስት ማረጋገጫ እንደሰጠው ባንኩ በመግለጫው አስታውቋል።

ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር መልካም ግንኙነት እንዳለው ያረጋገጠው ባንኩ ስለተፈጠረው ሁኔታ ግን ከመንግስት ጋር የሚያደርገው ግንኙነት መደበኛ የዲፕሎማሲ መንገዶችን የተከተለ መሆኑን ጠቁሟል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button