ባህል እና ጥበብዕለታዊፍሬዜና

ባህልና ጥበብ፡ ሰዋሰዉ መልቲሚዲያ ከአለም አቀፉ ግዙፍ የሙዚቃ ኩባንያ ዩኒቨርሳል ሚዩዚክ ግሩፕ (UMG) ጋር በጋራ ለመስራት ተስማሙ

አዲስ አበባ ህዳር 6/2016 ዓ/ም፦  ሰዋሰው መልቲሚዲያ ከዓለም አቀፉ የሙዚቃ ኩባንያ ዩኒቨርሳል ሚዩዚክ ግሩፕ (UMG) ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል ሥምምነት መፈራረሙን ለአዲስ ስታንዳርድ በላከው መግለጫ አስታውቀ።

ድርጅቱ በመግለጫው  “በሙዚቃዉ አለም የገነነ ስም ያላቸዉን ድምፃዉንን ሰብስቦ ከያዘዉ ዩኒቨርሳል ሚዩዚክ ግሩፕ (UMG) ጋር የተደረገው ስምምነት የሀገራችንን ድምፃዉያን በአለማቀፍ የሙዚቃ ገባያ ላይ ከማስቀመጥ ባለፈ ለሀገራችን ሙዚቃ እና በሙዚቃዎቻችን ዉስጥ የሚንፀባረቁ ባህሎቻችንን ከፍ አድርገን ለማሳየት ትልቅ በር የሚከፍት ይሆናል” ብሏል፡፡

ሰዋሰዉ መልቲሚዲያ እነ አስቴር አወቀን ፤ ቴዎድሮስ ካሳሁን ፤ አብነት አጎናፍር፤ ግርማ ተፈራ፤ ፀደንያ ገ/ማርቆስንን ጨምሮ በርካታ ድምፃዉያንን እና ሙዚቀኞችን በስሩ የያዘ ሲሆን የሀገራችንን ሙዚቃ የተቀላቀለው ከአንድ አመት በፊት ነው፡፡

ሰዋሰዉ መልቲሚዲያ ድምፃዉያን ፤ ገጣሚያን ፤ የዜማ ደራሲዎችና አቀናባሪዎች የለፉትን ልፋት ያማከለ ስራቸዉን በሚመጥን መልኩ ፕሮዲዩስ እያደረገ የሚገኝ ሲሆን ፤ በሰዋሰዉ አፕሊኬሽንም የድምፃዉያኑን ስራ ወደ ህዝብ እያደረሰ ይገኛል። 

በ1930ዎችሁ ወደ መዝናኛዉ ኢንደስትሪ የገባዉ እና ዛሬ ላይ ከ46 ቢሊዮን ዶላር በላይ በማንቀሳቀስ የአለምን የሙዚቃዉ ኢንደሰትሪን  የሚመራዉ ዩኒቨርሳል ሚዩዚክ ግሩፕም (UMG) ፤ በኢትዮጵያ ሙዚቃ ዉስጥ የሰዋሰዉን ፈጣን የሆነ አኪያሄድ እና አላማ ተመልክቶ ይህንን በሀገራችን በመዝናኛዉ ዘርፍ ታሪካዊ ሊባል የሚችልን ዉል መፈራረሙ ነው የተገለጸው። 

ከዛሬ ህዳር 6 ቀን ጀምሮ በዩኒቨርሳል ሚዩዚክ ግሩፕ (UMG) ፕሮዲዩስ የተደረጉ በሺዎች የሚቆጠሩ የአለም አቀፍ ድምፃዉያን ሙዚቃዎች በሰዋሰዉ አፕ ላይ ይገኛሉ ሲል ሰዋሰው አስታውቋል። 

ከዚህ ቀደም ድምጻዊ ሮፍናን ኑሪ ከዩኒቨርሳል ሚዩዚክ ግሩፕ (UMG) ጋር ለመስራት መስማማታቸው ይታወቃል፡፡ አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button