ዕለታዊፍሬዜናፖለቲካ

ዕለታዊ ዜና፡ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ሃላፊ አንቶኒ ብሊንከን ከጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ጋር በስልክ መውያየታቸው ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 8/ 2016 ዓ/ም፦ አንቶኒ ብሊንከን ከዶ/ር አብይ ጋር ባደረጉት የስልክ ውይይት ቀጣይ ወር በኢትዮጵያ ስለሚጀመረው የምግብ አርዳታ መምከራቸውን የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ቃል አቀባይ ቢሮ አስታውቋል። 

ብሊንከን የኢትዮጵያ መንግስት እና የሰብአዊ ዕርዳታ አጋሮች ለከፋ የምግብ ዋስትና ችግር ለተጋለጡ ወገኖች የምግብ እርዳታ መድረሱን ለማረጋገጥ ያደረጉትን ማሻሻያ አድንቀዋል።

አንቶኒ ብሊንከን እና ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በሰሜን ኢትዮጵያ ሰላምን ለማጠናከር በሚደረገው ጥረት እና የቀጠናዊ ትብብር አስፈላጊነት ላይም ተወያይተዋል ሲል ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ ቃል አቀባይ ቢሮው አስታውቋል።

በአማራ፣ በኦሮሚያ እና በሌሎች የሀግሪቱ አካባቢዎች እየተከሰቱ ያሉ ግጭቶች እንዳሳሰባቸው የገለጹት ሃላፊው ግጭቶችን ለመፍታት ውይይት እና ድርድር አስፈላጊ መሆኑንም አሳስበዋል ነው የተባለው።አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button