ዕለታዊፍሬዜናፖለቲካ

ዕለታዊ ዜና፡ የሱዳን ተፋላሚ አካላት የተኩስ አቁም ስምምነት ለማድረግ ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 1/ 2016 ዓ/ም፡ የሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ሊቀ መንበር ሌተናል ጄነራል አብደል ፈታህ አል ቡርሃን እና የፈጥኖ ደራሽ ኃይል መሪ መሀመድ ሀምዳን ዳጋሎ የተኩስ አቁም ስምምነት ለማደረግ ከስምምነተ ላይ መደረሳቸው ተገለጸ።

ውሳኔው ላይ የተደረሰው በጅቢቲው ፕሬዝዳንት እስማኤል ጉይለህ አዘጋጅነት በጅቢቲ በተካሄደው በ41ኛው የኢጋድ መሪዎች ጉባዔ ላይ ነው። 

የኢጋድ ዋና ጸሃፊ ወረቅነህ ገበየሁ ሁለቱ ወገኖች ባፋጣኝ ጦርነትን ለማቆም ስምምነት ላይ ለመደረስ በመስማማታቸው እንዳስደሰታቸው ገልፀው የሱዳንን ህዝብ ፍላጎት ለመመለስ ወሳኝ እርምጃ ነው ብለዋል።

በጉባዔው አል ቡርሃን ከዳጋሎ ጋር እንድገናኙ ለማሳመን ብርቱ ጥረቶች የተደረጉ ሲሆን ከበድ ያሉ የቃላት ለውውጦችም ተስተውለዋል። በተጨማሪም የኢጋድ መሪዎች  በሱዳን እየተከናወነ ያለውን ድርድር የሚያመቻቹ ልዩ መልእክተኞች ማቋቋማቸን ሱዳን ትሪቡን ዘግቧል።

ይህ ውሳኔ የሱዳንን ሰላም ለማረጋገጥ ወሳኝ እርምጃ መሆኑም ነው የተገለጸው። 

የሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ሊቀ መንበር ሌተናል ጄነራል አብደል ፈታህ አል ቡርሃን እና የፈጥኖ ደራሽ ኃይል መሪ መሀመድ ሀምዳን ዳጋሎ መካከል በመካሄድ ላይ የቆየው ግጭት እሰካሁን ከ10,ሺህ በላይ ሰዎች ተገድለዋል። በተጨማሪም 1.4 ሚሊየን ሰዎች ተፈናቅለዋል።አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button