ባህል እና ጥበብዕለታዊፍሬዜና

ዕለታዊ ዜና፡ ሩሲያ በኢትዮጵያ ባህሏን እና ቋንቋዋን የማስተዋውቅ መርሃግብር አካሄደች

አዲስ አበባ፣ ህዳር 7/ 2016 ዓ/ም፦ ሩሲያ በኢትዮጵያ ታሪኳን፣ ባህሏን፣ ቋንቋዋን እና ጂኦግራፊዋን የማስተዋውቅ ዝግጅት አካሄደች። 

የያሊያኖቭስክ መንግስት ፔዳጎጂካል ዩኒቨርሲቲ (ሩሲያ) ፋካልቲ አባላት የሩሲያ ታሪክ፣ ባህል እና ጂኦግራፊ ላይ ባህላዊ እና ትምህርታዊ ዝግጅቶችን በኢትዮጵያ አካሄደዋል።

ለአዲስ ስታንዳርድ በተላከው መግላጫ፤ ትምህርቱ ለተለያዩ የተማሪዎች (መምህራን እና ተማሪዎች) የተዘጋጀ ሲሆን በተለያዩ የልደታ ማርያም ልጃገርዶች ትምህርት ቤት እና በራሲያ የሳይንስና የባህል ማዕከል ተስጥቷል ነው የተባለው።

የትምህርት ካሪኩለሙ የተዘጋጀው በያሊያኖቭስክ መንግስት ፔዳጎጂካል ዩኒቨርሲቲ ፋካልቲ ሲሆን አላማው የሩሲያን ታሪክ፣ ባህል እና ጄኦግራፊ ለዋስታወቅ መሆኑ ተገልጿል፡፡ 

ተማሪዎቹ በቭርቹዋል (በምናብ) የሩሲያ ከተሞችን መጎብኘታቸውን፣ ስለ ሩሲያ ጦር እና ሰንደቅ አላማ እውቀትን ማግኘታቸው እና የብሔራዊ መዝሙሩን ማዳመጣቸው ተገልጿል።

በተጨማሪም ስለ ሩሲያ ታሪክ አዳዲስ እውነታዎችን እንዲርዱ መደረጉና ተማሪዎቹ ስለ ሀገሪቱ ታሪክ እና ታዋቂ ሰዎች ያላቸውን እውቀት በጥያቄና መልስ ተፈትኗል ተብሏል።አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button