ባህል እና ጥበብማህበራዊ ጉዳይ
በመታየት ላይ ያለ

ኩሌ(Khuullee): በርካቶችን እያከራከር የሚገኘው የላቲን ፊደላትን ለመተካት ታስቦ የተዘጋጀው አዲሱ የአፋን ኦሮሞ ፊደላት

አዲስ አበባ፣ ጥር 24/ 2016 ዓ/ም፦ ለረጅም አመታት በአገልግሎት ላይ ያለውን የአፋን ኦሮሞ የላቲን ፊደላትን ለመተካት “ኩሌ” በሚል ስያሜ የተዘጋጀው አዲሱ ፊደላት ሰሞኑን መነጋገሪያ ሆኖ ቆይቷል። 

ይህ “ኩሌ” የተባለው የአፋን ኦሮሞ ፊደላት የተዘጋጀው ከ19 አመታት በፊት ሲሆን እስከ አሁን ከአስር በላይ መጽሓፍት በፊደላቱ ተጽፈው ታትመዋል። የዚህ ፊደላት ቀራጺ የሆኑት ማስተር ሃሰን አብዱልቃዴ አዪሞ ከ5000 በላይ ተማሪዎችም በዚህ አዲሱ ፊደላት መማራቸውን እና የላቲን ፊደላት ያሉትን እጥረቶች የሚፈታ መሆኑን ለአዲስ ስታንዳርድ ገልጸዋል። በአዲሱ ፊደላት በሀረርጌ፣ ባሌ፣ ቦረና እና አርሲ የማሰተማር ተግባር ሲከወንበት መቆየቱንም አክለው ገልጸዋል።

የፊደላቱ አዘጋጅ የሆኑት ማሰተር ሀሳን አልዱላቃድር “ ፊደላቱ የተቀረጹት ከአረብ ውይም ከቻይና ፊደላት ሳይሆን ከኦሮሞ ባህላዊ እና ፍልስፍና እሴቶች የተቀዳ ነው” ሲሉ ገልጸዋል። 

ነባሩን የላቲን ፊደላትን ለመተካት ታስቦ የተዘጋጀው ይህ አዲስ ፊደላት (ኩሌ)፣ በአገልግሎት ላይ ያለው የአፋን ኦሮሞ ፊደላት ላይ የሚስተዋለውን ችግሮች ለማሻሻል ያለመ መሆኑን የገለጹት ማስተር ሀሰን “በአገልግሎት ላይ ያለው የላቲን ፊደላት ችግሮች አሉት፤ ኩሌን የቀረጽኩትም በዚሁ ምክንያት ነው” ብለዋል። 

ይህ አዲስ ፊደላት ከሚቀረፉት ችግሮች ውስጥ አንዱ በአፋን ኦሮሞ ውስጥ ያለው ድርብ ፊደላት ሲጥብቁ እና ሲላሉ የሚሰጡትን የተለያየ ትርጉም መለየት የማያስችሉ በመሆኑ ኩሌ ይህን ችግር ይፈታል ሲሉ ገልጸዋል። 

ከዚህ በተጨማሪም አዲስ ፊደላት ብስርዓተ ነጥብ አጠቃቀም ላይ የሚፈታችው ችግር መኖሩን እና የአፋን ኦሮሞን ቃላት ርዝማኔን ማሳጠር መቻሉን አክለው ተናግረዋል።  

ቀራጺው በፊደላቱ ጋዜጣን ጨምሮ በርካታ ጽሁፎች መታተማቸውን እና አሁንም ይህ አዲስ ፊደላት በጥናት ላይ መሆኑን ነው ያሰረዱት።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

“በዚህ ጉዳይ ላይ ምክክር ለማደረግ ከድሬ ደዋ እና ሀረመያ ዩኒቨርሲቶዎች ጋር ስምምነት አለን። በምምክር መድረኩ ከ 18 ዩኒቨርሲቲዎች መሁራንን አንድ ላይ በማምጣት ለመምከር ታቀዷል። በተጨማሪም አራት ሰዎች በጉዳዩ ላይ ጥናት እንዲያደርጉ ተመርጠዋል” ብለዋል። 

ጥናት እንዲያቀርቡ ከተመረጡት ሰዎች መካከል አንዱ በወለጋ ዩኒቨርሲቲ የአፋን ኦሮሞ ረዳት ፕሮፌሰር የሆኑት ፌደሳ ታደሰ ሲሆኑ በዩኒቨርሲቲው ጥናታዊ ጽሁፍም አቀረበዋል።  

በአዲሱ ፊደላት ላይ ጥናታዊ ጽሑፋቸውን ያቀረቡት ረዳት ፕሮፌሰር ፌደሳ ታደሰ፤ ኩሌ ፊደላት ዝግጅት በጣም በሳል ሆኖ ስላገኘሁት ፊደላቱን መርጬ ጥናት አድርጊያለው ሲሉ ገልጸዋል። ጥናቱን መጨረሳቸውን የገለጹት ረዳት ፕሮፌሰሩ ምሁራን ሊወያዩበት ይችላሉም ብለዋል። 

ይሁን እንጂ ይህን አዲሱን ፊደላት የተቹ ምሁራንም ቀላል አይደሉም። የአፍሪካ ቋንቋዎች ድርጅት የቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት ፕሮፌሰር ቶሎሳ ሶሬሳ “ “ለአፋን ኦሮሞ አዲስ ፊደላት መቅረጽ አስፈላጊ አይደለም። አፋን ኦሮሞ ከድርብ ፊደላት ጋር ተያይዞ ችግር የለውም። ኢንግለዝኛን ጨምሮ በርካታ ቋንቋዎች የራሳቸው ችግሮች አሏቸው። አፋን ኦሮሞ ውስጥ እጥረት ካለ የሚሻለው ለችግሮቹ መፍትሄ እየፈለጉ መሄድ እንጂ አዲስ ፊደላት መቅረጽ ምላሽ አይሆንም” ብለዋል።

በተጨማሪም የአይቲ በለሙያ የሆነው አብዲስ ባንቻ አዲሱን ፊደላት ከተቹ ሰዎች መካከል ሌላኛው ግለሰብ ነው። አብዲሳ ኩሌ በቋንቋው እድገት ላይ ተጽዕኖ እንዳለው አስታየቱን ገልጿል። 

ነገር ግን የኩሌ ቀራጺ ማስተር ሀሰን በተነሳው ነቀፌታ ላይ “ የሚነቅፉ ሰዎች ለአፋን ኦሮሞ ካላቸው ተቆርቋሪነት የተነሳ መሆኑን እረዳለው። ነገር ግን ኩሌን ሳያነቡ መንቀፍ ትክክል አይደለም ብለዋል።” አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button