ዜናቢዝነስ

ዜና፡ በሁለት ነዳጅ ጫኝ መርከቦች የተቀየረችው ዓባይ፪ የተሰኘች ግዙፍ መርከብ ለመጀመሪያ ጊዜ የኢትዮጵያን ጭነት ይዛ ጅቡቲ ደረሰች ተባለ

አዲስ አበባ፣ ጥር 24/2016 ዓ.ም፡- የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ በቅርቡ ድርጅቱን ለኪሳራ ዳርገው ነበር ያላቸው እና 42 ሺ ሜትሪክ ቶን የመጫን አቅም ባላቸው ሁለት ነዳጅ ጫኝ መርከቦች የቀየራት ዓባይ ፪ የተሰኘች መርከቡ ጅቡቲ መድረሷ አስታወቀ።

ዓባይ ፪ 60 ሺ ሜትሪክ ቶን ኤን. ፒኤስ እና ኤን.ፒኤስ.ቢ የአፈር ማዳበሪያ ዓይነቶችን ነው ከሞሮኮ ጆርፍ ላስፈር ወደብ ወደ ጅቡቲ ያመጣችው ብሏል፡፡

በግዙፍነቷም ሆነ በዓይነቷ የመጀመሪያ የሆነችው ዓባይ ፪ መርከብ በኢትዮጵያ ባንዲራ ተመዝግባ ወደ አገልግሎት ከገባችበት ጊዜ ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ የኢትዮጵያን የአፈር ማዳበሪያ ጭነት ይዛ ትናንት ጥር 23 ቀን 2016 ዓ.ም. ጅቡቲ ወደብ ደርሳለች ሲል ተቋሙ በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ በጋራው መረጃ ገልጿል።

ቀደም ሲል በውጭ ሀገራት መርከቦች ኪራይ ሲከናወን የነበረው የአፈር ማዳበሪያ ጭነት ቀይ ባህር አካባቢ ከተከሰተው የደህነት ስጋት አኳያ ወደ አካባቢው ላለመጓዝ በመወሰናቸው የተነሳ ችግር ላይ ይወድቅ የነበረውን የአፈር ማዳበሪያ የማጓጓዝ ተግባር በራሳችን መርከብ ዓባይ ፪ ማጓጓዝ ችለናል ብሏል።

መርከቧ በአሁኑ ሰዓት በጊዜያዊ የኪራይ ኮንትራት /Time Charter/ አገልግሎት ተሰማርታ በአውሮፓ፣ በኤዥያ እና በአፍሪካ አህጉራት ባሉ ወደቦች መካከል የሌሎች ሀገራት ጭነቶችን በማጓጓዝ የውጭ ምንዛሬ ገቢ እያስገኘች ነው ሲል ጠቁሟል፡፡

የምርት ዘመኑን የአፈር ማዳበሪያ በባሕር አጓጉዞ እስከ ጅቡቲ የሚያደርሰው ስካይ ፍዩዥን (Sky Fusion) የተባለ ዓለም-አቀፍ የመርከብ ድርጅት መሆኑን እና ዓባይ ፪ መርከብም ለዚሁ ድርጅት በጊዜያዊነት ተከራይታ ያለች በመሆኑ ነው ይህን ጭነት ይዛ ልትመጣ የቻለቸው ብሏል፡፡ በቀጣይ መርከቧ የኮንትራት ጊዜዋን ስታጠናቅቅም የሀገራችንን ጭነት ወደ ማጓዝዝ ስራ ትሰማራለች፡ ሲል ገልጿል፡

በመጪዎቹ ሁለት ሳምንታት 73 ሺ 800፣ 83ሺ 400 እና 51 ሺ ሜትሪክ ቶን አፈር ማዳበሪያ የጫኑ ግዙፍ መርከቦች ጅቡቲ እንደሚደርሱ መረጃው አመላክቷል። አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button