ዜና

ዜና፡ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ማራዘሙን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 24/ 2016 ዓ/ም፦ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት በአማራ ክልል የታወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማራዘሙን አስታወቀ።

ምክር ቤቱ አዋጁን ያራዘመው ዛሬ ጥር 24 ፣ 2016 ዓ.ም በተካሄደው 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ ልዩ ስብሰባ ነው።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሐምሌ 28 ቀን 2015 ዓ.ም ባካሄደው 23ኛ መደበኛ ስብሰባ በአማራ ክልል የተከሰተው “በትጥቅ የተደገፈ እንቅስቃሴ” በመደበኛ የህግ ማስክበር ስርዓት ለመቆጣጠር ወደ ማይቻልበት ደረጃ የተሸጋገረ በመሆኑ የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ማወጁ ይታወሳል።

በዛሬው ስብሰባ የውሳኔ ሀሳቡን ረቂቅ ያቀረቡት የፍትህ ሚንስትሩ ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር) በአዋጁ መራዘም አስፈላጊነት ላይ ማብራሪያ ማቅረባቸውን ተከትሎ የምክር ቤቱ አባላት ሰፊ ውይይት አድርገዋል ተብሏል። ነገር ግን ምክር ቤቱ በአዋጁ መራዘም አስፈላጊነት ላይ የቀረበውን ማብራሪያ ይፋ አላደረገም።

ምክር ቤቱ የቀረበለትን የውሳኔ ሀሳብ በውሳኔ ሀሳብ ቁጥር 5/2016 ሆኖ  በ ሁለት ተቃውሞ ፣ በሦስት ድምፀ ታዐቅቦ በአብላጫ ድምጽ አዋጁ አንዲራዘም አፅድቋል።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን መራዘም ተከትሎ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈፃፀም መርማሪ ቦርድ የስራ ዘመንን ለማራዘም የቀረበለትን የውሳኔ ሀሳብ የውሳኔ ቁጥር 6/2016 ሆኖ በ2 ተቃውሞ በአብላጫ ድምጽ አፅድቋል።

የክልሉ መንግስት በክልሉ የተቀሰቀሰው የትጥቅ ትግል ከክልሉ አቅም በላይ መሆኑን በመግለጽ የፌደራል መንግስቱ ጣልቃ እንዲገባ በጠየቀው መሰረት የታወጀውን አስቸኳይ ግዜ አዋጅ ስድት ወራትን አስቆጥሯል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

አዋጁ መታወጁን ተከትሎ በአማራ ክልል ያለው ሁኔታ “ህገ መንግስታዊ ሥርዓቱን አደጋ ላይ የጣለ በመሆኑ” ተጠሪነቱ ለጠ/ሚኒስትሩ የሆነ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የሚያስፈፅም በብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጄነራል የሚመራ የአስቸኳይ ጊዜ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝም መቋቁዋሙ ይታወቃል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button