ዜናፖለቲካ

ዜና፡ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ከአፍሪካ አገራት ጋር በትብብር ለመሥራት ዝግጁ መሆኑን ሌተናል ጀነራል ይልማ መርዳሳ ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 4/2016 .ም፡ የኢትዮጵያ አየር ኃይል በሁሉም ዘርፎች ከአፍሪካ አገራት ጋር በትብብር ለመሥራት ዝግጁ መሆኑን በቢሾፍቱ በመካሄድ ላይ ባለው የመጀመሪያው የአፍሪካ አየር ኃይል አዛዦች ፎረም ላይ ሌተናል ጀነራል ይልማ መርዳሳ ገለጹ።

በቢሾፍቱ እየተካሄደ በሚገኘው የአፍሪካ አየር ኃይል አዛዦች ፎረም ላይ የአፍሪካ አገራት አየር ኃይል አዛዦች፣ የተለያዩ አገራት የአቪዬሽን ተቋማት ኃላፊዎችና ወታደራዊ አታሼዎች መገኘታቸውም ተጠቁሟል።

በፎረሙ በአፍሪካ የአየር ኃይል ዕድገት ላይ ሊገጥም የሚችሉ ተግዳሮቶችን በጋራ መፍታት በሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች ዙሪያ ምክክር ይደረጋል ተብሏል።

የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጀነራል ይልማ መርዳሳ አየር ኃይሉ በርካታ የአፍሪካ አገራትን በአየር ኃይል፣ በልምምድና በአየር ትራንስፖርት ዘርፎች እገዛ ሲያደርግ እንደነበር በፎረሙ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር ጠቁመው ይህንንም አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

የኢትዮጵያ አየር ኃይል በቀጣይም የጀመራቸውን ሥራዎች ይበልጥ በማጠናከር በሁሉም ዘርፎች ከአፍሪካ አገራት ጋር በትብብር ለመስራት ዝግጁ መሆኑ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ አየር ኃይል 88ኛ ዓመት የምስረታ በዓል “በመስዋዕትነት አገርን የዋጀ የኢትዮጵያ አየር ኃይል” በሚል መሪ ኃሳብ ከሕዳር 20 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተከበረ ይገኛል። አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button