ማህበራዊ ጉዳይ

ዜና: በአማራ ክልል የሚገኙ ሱዳናውያን ስደተኞች ሁኔታ አሳስቦኛል ሲል የመንግስታቱ ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ኮሚሽን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 21/2016 ዓ.ም፡- በአማራ ክልል “ከአውላላ የስደተኞች መጠለያ” ወጥተው በአቅራቢያው በሚገኝ መንገድ ዳር መኖር የጀመሩ የሱዳናውያን ስደተኞች ሁኔታ እንዳስጨነቀው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ኮሚሽን ባወጣው መግለጫ አስታወቀ።

ሱዳናውያኑ ስደተኞች በአውላላ መጠለያ አቅራቢያ መንገድ ዳር መኖር ከጀመሩ ሶስት ሳምንታት እንዳለፋቸው ጠቁሟል።

በአማራ ክልል ከሚገኝ የመጠለያ ጣቢያ ተጠልለው ከሚገኙ ስደተኞች መካከል አንድ ሺ የሚጠጉ ሱዳናውያን ስደተኞች በተከታታይ በሚደርስባቸው ጥቃት አና የጸጥታ ቸግር ሳቢያ መጠለያ ካምፑን ጥለው ሚያዚያ 23 ቀን 2016 ዓ.ም መውጣታቸው ኮሚሽኑ አስታውሷል።

መጠለያ ካመፑን ጥለው ከወጡት መካከል የተወሰኑት በረሃብ አድማ ላይ መሆናቸውን የጠቆመው ኮሚሽኑ በአከባቢው ያለው ተለዋዋጭ እና አስጊ ሁኔታ ከረሃብ አድማው ጋር ተደምሮ እንዳሳሰበው አስታውቋል።

ኮሚሽኑ ከፌደራል መንግስቱ የስደተኞች እና ስደት ተመላሽ አገልግሎት ጋር በመሆን የስደተኞቹን ጥያቄ ለመስማት እና መፍትሔ ለማበጀት መጣሩን ገልጿል።

ስደተኞቹ የሚያቀርቡት ጥያቄ እና የተፈጠረባቸው ስጋት አግባብነት ያለው መሆኑን ገልጾ በመንገድ ዳር ምንም አይነት መሰረታዊ አገልግሎት በሌለበት በማካሄድ ላይ ያሉት ተቃውሞ ለባሰ አደጋ የሚያጋልጥ በመሆኑ ስጋት እንዳደረበት አስታውቋል።

ከመጠለያ ካምፑ በመውጣት በመንገድ ዳር ላይ የሚገኙትን ስደተኞች ለማገዝ ጥረት እያደረገ መሆኑን የጠቆመው ኮሚሽኑ በተመሳሳይ የአከባቢው ባለስልጣናት ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ጥበቃ እያደረጉላቸው መሆኑን አስታውቋል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

በአከባቢው ያለው የጸጥታ ሁኔታ እጅግ አስጊ እና ፈታኝ መሆኑን በመጠቆም ከአውላላ የስደተኞች መጠለያ አቅራቢያ ባለፈው ሳምንት አርብ ግንቦት 16 ቀን 2016 ዓ.ም የረድኤት ሠራተኞችን አሳፍሮ ሲጓዝ በነበረ ተሽከርካሪ ላይ በተተኮሰ ጥይት አንድ ሰራተኛ መገደሉን በማሳያነት ጠቅሷል።

በዚህም ሳቢያ በአከባቢው እንቅስቃሴ ማድረግ ተገድቦ የነበረ ቢሆንም ትላንት ግንቦት 20 ቀን 2016 እንደገና መንገዱ ክፍት መደረጉን ጠቁሟል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button