ፖለቲካ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና: የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ “በተለያዩ እስር ቤቶች የሚገኙ የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪዎችን” ጨምሮ ለስምንት አካላት የዕውቅና ሽልማት አበረከተ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23/2016 ዓ.ም፡- በአዲስ አበባ የሚገኘው የአውሮፓ ህብረት በሀገሪቱ የተለያዩ እስር ቤቶቸ የሚገኙ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችን ጨምሮ ለስምንት ግለሰቦች እና ተቋም የአመቱን የህብረቱን የሹመን የሰብአዊ መብት ሽልማትን (EU Schuman Human Rights Award) አበረከተ።

በሀገሪቱ የሰብአዊ መብት እንዲከበረ እና ድምጽ ለሌላቸው ድምጽ በማሰማት አስተዋጽኦ አበረክተዋል በሚል ስድስት ግለሰቦች የተሸለሙ ሲሆን ከነዚህ ውስጥም የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ይገኙበታል፤ ተቋማቸውን አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ እንዲሆን አስችለዋል የሚል አድናቆት ተችሯቸዋል።

በሌሉበት እና በስነስረአቱ ላይ ያልተገኙት ፈልገው ሳይሆን ሰብአዊ መብት ተሟጋቾች በመሆናቸው ብቻ በተለያዩ የሀገሪቱ ማጎሪያ ቦታዎች እና እስር ቤቶች ላይ በመሆናቸው ነው በሚል የተገለጹ ኢትዮጵያውያን የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪዎች ሽልማቱ ተበርክቶላቸዋል።

 “በተለያዩ እስር ቤቶች ለሚገኙ የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪዎች” ተብሎ የተሰጠው ሽልማት በአዲስ አበባ በሚገኘው የህብረቱ ቢሮ በግልጽ በሚታይ ቦታ ይቀመጣል ተብሏል።

በአዲስ አበባ በሚገኘው የህብረቱ ልዑክ ቅጥር ግቢ በተካሄደ ስነስርአት ሽልማቱን በኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት አምባሳደር የሆኑት ሮላንድ ኮብያ አበርክተዋል፣ የህብረቱ ሀገራት ከፍተኛ ሃላፊዎች ታድመዋል።

በሽልማቱ ስነስርአት ወቅት ንግግር ያደረጉት በኢትዮጵያ የህብረቱ አምባሳደር፣ ሽልማቱ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ግዜ የተሰጠ መሆኑን በመግለጽ እንደባህል በየአመቱ በኢትዮጵያ ሽልማቱ በቀጣይ አመታት ይተገበራል የሚል ተስፋ እንዳላቸው ጠቁመዋል።

በኢትዮጵያ ስላለው የሰብአዊ መብት አከባበር ምንም ያላሉት አምባሳደሩ ህብረቱ ለሰብአዊ መብት መከበር ትኩረት እንደሚሰጥ በመጠቆም ከተለያዩ ሀገራት ጋር የሚደረጉ የህብረቱ የንግድ ስምምነቶች ጭምር የሰብአዊ መብት መከበር አጀንዳ መሆኑን አስታውቀዋል። የሰብአዊ መብት መከበር የንግድ ግንኙነታችን አንዱ መስፈርት ነው ሲሉ ገልጸዋል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ፣ የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ያሬድ ሃ/ማርያም፣ በሶማሌ ክልል የሚንቀሳቀሰው የሆርሙድ የሴቶች ማህበር ሊቀመንበሯ ጋሪ ኢስማኤል ዩሱፍ፣ የአፍሪካ ቀንድ የሰብአዊ መብቶች ሊግ መሥራች ጌቱ ሳከታ፣ ከሰብአዊ መብት በተጨማሪ በአከባቢ ጥበቃ ተቆርቋሪ መሆኑ የተገለጸው የቁም ለአካባቢ ሊቀ-መንበር መልካሙ ኦጋ፣ የኢትዮጵያ ሴት የህግ ባለሞያዎች ማህበር፣ የፈንዲቃ የባህል ማዕከል መሥራች የሆነው አርቲስት መልካሙ በላይ እና በእስር ላይ የሚገኙ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ሽልማቱ የተበረከተላቸው ናቸው።

ሽልማቱ የተበረከተው ለስድስት ግለሰቦች ለአንድ ተቋም እና በአዲስ አበባ በሚገኘው የህብረቱ መስሪያ ቤት ከፍ ብሎ ይቀመጣል ለተባለው እና እንደ ግለሰብም ይሁን እንደተቋም ሽልማቱ ያልተሰጠው በማጎሪያ ቤቶች ላሉ ለእስር የተዳረጉ ኢትዮጵያውያን የተበረከተ ሌላው ሽልማት ነው።

እንደ ተቋም ሽልማቱ የተበረከተው ለኢትዮጵያ ሴት የህግ ባለሞያዎች ማህበር ሲሆን ለሽልማት ያበቃውም ለሶስት አስርት አመታት ለሚጠጋ በሀገሪቱ የሴቶች መብት እንዲከበር ላበረከተው አስተዋጽኦ መሆኑን በሽልማቱ ስነስርአት ላይ ተገልጿል።

ሽልማቱ ከተበረከተላቸው በኋላ ስድስቱ ግለሰቦች እና የኢትዮጵያ ሴት የህግ ባለሞያዎች ማህበር፣ ተወካይ ባደረጉት ንግግር በሀገሪቱ የሰብአዊ መብቶች እንዲከበሩ የሚያደርጉትን ጥረት አጠናክረው እንዲቀጥሉ የሚያበረታታን ነው ሲሉ ገልጸዋል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button