ማህበራዊ ጉዳይዜና
በመታየት ላይ ያለ

ዜና፡ በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ሰሀላ ሰዬምት ወረዳ በተከሰተ ድርቅ የሁለት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በሰሜን ጎንድር 16 ሰዎች በረሃብ ምክንያት ሞተዋል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 18/ 2015 ዓ.ም፡- በአማራ ክልል በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ሰሀላ ሰዬምት ወረዳ ክረምት ዝናብ ባለመዝነቡ በተከሰተ ድርቅ የሁለት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በተመሳሳይ መልኩ በሰሜን ጎንድር ዞኖች በተከሰተ ድርቅ በጃናሞራ ወረዳ 16 ሰዎች በረሃብ ምክንያት መሞታቸው ተገለፀ፡፡

በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ሰሀላ ሰዬምት ወረዳ በሚገኙት በአስራ ሶስቱም ቀበሌዎች በተከሰተ ድርቅ አጠቃላይ ካለው ከ52 ሺህ በላይ ህዝብ ውስጥ 46ሺ የሚሆነው አፋጣኝ እርዳታ ካለገኘ ከባድ አደጋ ውስጥ እንደሆነ የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ሲሳይ ብሩ ተናግረዋል

አስተዳዳሪው የወረዳው አስከፊነት ሲገልፁ “እንስሳት ቆዳቸው ከስጋቸው መጣበቅ ብቻ ሳይሆን ነፍሳቸው በጣዕረሞት ላይ እንደሆነች ተመለከተናል፣ ህጻናት፣ እናቾችና አረጋውያን በርሀብ ተገርፈው ነፍሳቸው ከጉንጫቸው ተጣብቃ ይዛቸው ልትጠፋ አፋፍ ላይ እንደሆነች ቆመን አየን፤ ብቻ ተሎ ካልደረስን አሳዛኝ ክስተት በሰሀላ ሰዬምት ወረዳ ሊከሰት እንደሚችል ተረድተናል” ብለዋል።

አቶ ሲሳይ  አክለውም “ምንም እንኳን ድርቅ ቢሆንም ከዚህ በፊት ለእንስሳት የሚሆን ሳር አይጠፋም ነበር። ዛሬ ግን የተቃጠለ መሬት ብቻ ነው የሚታየው፤ ለጥርስ ስጋ ማውጫ የሚሆን የሳር ስንጥር እንኳን አይታይም፤ በወረዳችን እንዲህ አይነት ድርቅ አይተን አናውቅም፤ የሰባ ሰባቱ ድርቅ እንኳን አንዲህ አልነበረም” ብለዋል ሲል የዋግ ኽምራ ኮሚዩኒኬሽን ገልጧል፡፡

ነዋሪዎቹ በበኩላቸው “በዚህ ሳምንት ውስጥ የሚበላ ካልቀረበ ልጆቻችን አናገኛቸውም አሁንም ቢሆን አንዲት እንጀራ ለ10 ሰው ነው የምንሻማው፤ ከዛ ውጭ ግን ጨው በውሀ በጥብጠን ነው የምንጠጣው” ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ተጠሪ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ምህረት መላኩ እንደሰጡን መረጃ የተለያዩ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ቃል ከመግባት የዘለለ በመንግስት በኩል ምንም የቀረበ ነገር የለም። ለክልሉ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ተጠሪ ጽ/ቤት ሪፖርት ከማድረግ ባለፈ የችግሩን አሳሳቢነት ብንገልጽም እስካሁን የተሰጠ ምላሽ የለም ብለዋል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

በተመሳሳይ መልኩ በክልሉ ሰሜን ጎንደር ዞን የክረምት ዝናብ ባለመዝነቡ በተከሰተው ድርቅ በጃናሞራ ወረዳ የ16 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ሸጋው ተሰማ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ከሟቾቹ መካከልም አብዛኞቹ ሴቶች እና አረጋውያን መሆናቸውንም ገልጸዋል።

የአካባቢው ባለስልጣን ለሚዲያው እንገለፁት በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር እና በሰሜን ጎንደር ዞኖች ከ10 ሺህ በላይ የዳልጋ እና የጋማ ከብቶች ሞተዋል።

“አርሶ አደሮቹ ተስፋ ቆርጠዋል። እስካሁን ድረስ ወደ 4 ሺህ የሚደርሱ አርሶ አደሮች የሄዱበት አልታወቀም። ስንንቀሳቀስ ቤታቸው ተዘግቶ ነው የምናገኘው። በአካባቢው ያሉት ነዋሪዎችም መንግሥት በአፋጣኝ እንዲደርስላቸው ተማጽነዋል” ብለዋል።

በአካባቢው አተትን ጨምሮ ወረርሽኞች በስፋት መከሰታቸውን አስተዳዳሪው ገልጸዋል።አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button