ዜናፖለቲካ

ዜና፡ በሃማስ እና እስራኤል መካከል በተቀሰቀሰው ጦርነተ ሁለት ትውልደ ኢትዮጵያውያን መሞታቸው ተሰማ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29/ 2016 ዓ.ም፡- በእስራኤልና ፍልስጤም መካከል በተቀሰቀሰው ጦርነት ሁለት ትዉልደ ኢትዮጵያዊያን መሞታቸዉን ብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን በእስራኤል ከሚገመኙ ምንጮቹ ማረጋገጡን ዘገበ።

የፖሊስ ሀይል አባል ነበር የተባለዉ ኦርኤል አብርሃም እና የሀገሪቱ ጦር አባል የነበረዉ ሳሙኤል ጎሊማ በጦርነቱ የተገደሉ ትውልደ ኢትዮጵያውያን የእስራኤል ዜጎች መሆናቸው በዘገባው ተገልጧል፡፡

የፖሊስ አባል የነበረዉ የኦርኤል አብርሃም ባለቤት በማህበራዊ የትስስር ገጿ ላይ የባለቤቷን መገደል አረጋግጣ አስክሬኑን የጸጥታ አካላት እንዲያፈላልጉላት ተማጽናለች ነው የተባለው። ሌላኛዉ የሀገሪቱ ጦር አባል ሳሙኤል ጎሊማም በጦርነቱ ከሐማስ ታጣቂዎች ጋር በነበረ ዉጊያ መሰዋቱ ተነግሯል።

እስካሁን ባለዉ መረጃም ሁለት ትዉልደ ኢትዮጵያዊያን መገደላቸዉ የተረጋገጠ ሲሆን ሌሎች የታገቱ እና የተገደሉ ሊኖሩ እንደሚችሉ እና የጠፉ ሰዎችን ማንነት የሚያጣራ ኮሚቴ መዋቀሩን ምንጮቹ ነግረውኛል ሲል ብስራት ሬዲዮና ቲቪ ዘግቧል።

አራተኛ ቀኑን በያዘው የእስራኤል- ሃማስ ጦርነት እስካሁን በሁለቱም ወገን የተገደሉ ሰዎች ቁጥር ከ1600 በላይ መድረሱን የውጭ ዜና ምንጮች ዘግበዋል፡፡ ከዚህ ውስጥ ከ900 በላይ የሚሆኑት የእስራኤል ዜጎች ሲሆኑ 140 ህፃናትን ጨምሮ ከ700 በላይ የሚሆኑት ደግሞ የፍልስጤም ዞጎች ናቸው ተብሏል፡፡

ነገር ግን የእስራኤል መከላከያ በበኩሉ 1500 የሚሆኑ የሃማስ ተዋጊዎች አስክሬን በጋዛ ሰርጥና እስራኤል መግኘቱንን አስታውቋል፡፡

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

እስራኤላዊያን ቅዳሜ እለት እያከበሩት በነበረው ሱፕረኖቫ ፌስቲቫል ላይ ሃማስ በከፈተው ጥቃት 260 የበዓሉ ተካፋዮች ህይወታቸውን አጥተዋል ነው የተባለው፡፡

እስራኤል በአንድ ምሽት ብቻ በጋዛ የመኖሪያ ህንፃዎችን ጨምሮ 200 ቦታዎች ላይ ከባድ  የአይር ጥቃት መፈፀሟን ተከትሎ ሃማስ በእገታዬ ስር የሚገኙትን የእስራኤል ዜጎች መግደል ጀምራለው ሲል አስጠንቅቋል፡፡አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button