ዜናጤና

ዜና፡ የአለም የጤና ድርጅት ባለፉት ዘጠኝ ወራት አንድ ሺ ሜትሪክ ቶን የሚጠጋ የህክምና እርዳታ ለትግራይ ማድረሱን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 15/2016 .ም፡ በትግራይ ለሚገኙ የህክምና ተቋማት 956 ሜትሪክ ቶን የህክምና አርዳታ ማድረሱን የአለም የጤና ድርጅት አስታወቀ። የህክምና እርዳታዎቹ የተሰጡት ባለፉት ዘጠኝ ወራት መሆኑን የጠቆመው ድርጅቱ በተጠቀሰው ግዜ ሁለት ሚሊየን የሚጠጉ የክልሉ ነዋሪዎች የህክምና አገልግሎት እንደተሰጣቸው አመላክቷል።

911ሺ የሚሆኑ በተለያዩ በሽታዎች የተጠቁ የክልሉ ነዋሪዎች የህይወት አድን የህክምና አገልግሎት በ28 የድርጅቱ አጋር ተቋማት እንደተሰጣቸው አስታውቋል። በጦርነቱ ሳቢያ የወረርሽኝ መከላከል እርምጃዎች በመቋረጣቸው ምክንያት ኮሌራ እና ኩፍኝ ወረርሽኞች የመስፋፋት እድላቸው ከፍተኛ ነው ሲል አስጠንቅቋል።

በክልሉ በከፍተኛ ደረጃ በመወርሽኝ መልክ ሊከሰት የሚችል በሽታ የወባ በሽታ መሆኑን ያመላከተው የጤና ድርጅቱ ባፉት ዘጠኝ ወራት ብቻ 204ሺ 398 ሰዎች በወባ በሽታ መያዛቸውን በማሳያነት አስቀምጧል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button