ዜናፖለቲካ

ዜና፡ የኤርትራ ጦር ያለአግባብ ከያዛቸው የኢትዮጵያ ግዛቶች ሙሉ በሙሉ ለቆ እንዲወጣ የአውሮፓ ህብረት ጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16/2016 .ም፡ በኢትዮ ኤርትራ የድንበር ኮሚሽን ውሳኔ መሰረት የኤርትራ ጦር ከኢትየጵያ ግዛቶች ለቆ እንዲወጣ የአውሮፓ ህብረት ጠይቋል። 78ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ጋር በተያያዘ ህብረቱ ባወጣው መግለጫ የኤርትራ ሰራዊት በንጹሃን ላይ ፈጽሞታል የተባለውን ሰብአዊ መብት ጥሰት ላይ ገለልተኛ ምርመራ እንዲካሄድ አሳስቧል።

ገለልተኛ ምርመራ መደረጉ በትግራይ ተካሂዶ በነበረው ጦርነት ወቅት ጉዳት የደረሰባቸው በትግራይ እና ከትግራይ ውጭ የሚገኙ ተጎጂዎች ፍትህ እንዲያገኙ ያስችላል ብሏል።

ህብረቱ በመግለጫው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኤርትራ ራፖርተር ባወጣው ሪፖርት መሰረት በርካታ ኤርትራውያን በዘፈቀደ እንደሚታሰሩ መገለጹ እና በርካቶችም የደረሱበት እንደማይታወቅ መካተቱ አሳስቦናል ብሏል።  

የኤርትራ መንግስት የት እንደደረሱ የማይታወቁ ዜጎቹ ያሉበትን እንዲያስውቅ የጠየቀው መግለጫው በእስር ላይ ያሉ ኤርትራውያንም እንዲለቀቁ አሳስቧል።

የኤርትራ መንግስት የሚያካሂደውን የህጻናት ሀገራዊ የወታደራዊ አገልግሎት ስርአት እንዲያቆም ህብረቱ በመግለጫው ጠይቋል።  

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button