ዜናፖለቲካ

ዜና፡ በአማራ ክልል እየተባባሰ የመጣውን ግጭት ለመፍታት የኢትዮጵያ መንግስት የሰላም ድርድር ማደረግ እንዳለበት ክራይስስ ግሩፕ አሳሰበ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 7/ 2016 ዓ/ም፦ ትኩረቱን በአለም አቀፍ ቀውስ ላይ ያደረገው ክራይስስ ገሩፕ አዲስ ባወጣው ሪፖርት የኢትዮጵያ መንግስት በአማራ ክልል እየተባባሰ የመጣውን ግጭት ለመፍታት የሰላም ድርድር መጀመር እንዳለበት አሳሰበ።

በአማራ ክልል በተቀሰቀሰው የትጥቅ ትግል መንግስት ከፍተኛ የጸጥታ ስጋት እያጋጠመው መሆኑን ሪፖርቱ አመላክቷል፡፡ ይህንን አለመረጋጋት ለመፍታት፣ ባለስልጣናት ግጭቱን በማባባስ ላይ ያለውን ጉዳይ በቀጥታ እንዲፈቱ፣ ዓለም አቀፉ ክራይስስ ግሩፕ ጥሪ አቅርቧል።

ተቋሙ በአማራ ክልል በመካሄድ ላይ ያለው ግጭት የመነጨው፣ በኢትዮጵያ በሚገኙ ብሄረሰቦች መካከል ካለው ውስብስብ ቅሬታ መሆኑን ጠቅሶ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በ2011 ዓ/ም ስልጣን ከያዙ ብሁዋላ ይህንን ጉዳይ ለምፍታት ሲጥሩ ነበር ብሏል፡፡

ክራይስስ ግሩፕ በትግራይ ሲካሄድ የነበረው ጦርነት በሰላም ስምምነት ከአመት በፊት መቋጨቱን አስታውሶ በጦርነቱ ከፌዴራል መንግስት ጎን ቆመው የትግራይ ሃይሎች ላይ ሲዘምቱ የነበሩ የአማራ ክልል ግለሰቦች፣ ከሰላም ስምምነቱ በሁዋላ እንደተካዱ ተሰምቷቸዋል ብሏል፡፡ በትግራይ ጦርነት ወቅት የተሰማሩ የአማራ ሚሊሻዎችን የፌደራል መንግስት ለመቆጣጠር መሞከሩ ውጥረቱን ማባባሱን አስታውቋል፡፡

በአማራ ክልል የተቀሰቀሰው ግጭት ሌሎች ያልተፈቱ ቀውሶችን እንደሚያወሳስብም ነው ሪፖርቱ ያስጠነቀቀው። በተለይ በኦሮሚያ ክልል የቀጠለው አመፅ፣ በትግራይ የሰላም ስምምነት አሁንም ያልተቋጩ ሂደቶች እና በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል ያለው ግንኙነት ከወደብ ተጠቃሚነት ጋር ተያይዞ እየሻከረ መምጣቱን በምሳሌነት አስቀምጥዋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ በአማራ ክልል ያለው ግጭት በአማራ እና በኦሮሞ ብሄረሰቦች መካከል ያለውን ውጥረት እንዳባባሰው ሪፖርቱ አመልክቷል። በአሁኑ ውቅት በርካታ የአማራ ነዋሪዎች የፌደራል መንግስት ባለስልጣናት በክልሉ በሚገኙ ንጹሃን ላይ በኦሮሞ ታጣቂዎች የሚደርሰውን ጥቃት መቆጣጠር አልቻሉም በማለት አየተቃወሙ ነው ሲል ክራይስስ ግሩፕ ገልጿል፡፡

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

በክራይሲስ ግሩፕ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ተንታኝ የሆኑት ዊሊያም ዴቪሰን፣ የኢትዮጵያን የረዥም ጊዜ ውስብስብ አለመግባባቶች መፍታት አስቸጋሪ መሆኑን ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሁን እያጋጠሟቸው ያሉ ችግሮችን ለመፍታት የአጭር ጊዜ እና የረዥም ጊዜ ስትራቴጂ ስልቶችን ማዘጋጀት እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button