ማህበራዊ ጉዳይዜና
በመታየት ላይ ያለ

ዜና፡ በትግራይ አበርጌሌ የጪላ እና አጽቢ ወረዳ በተከሰተው ድርቅ ምክንያት የ190 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 19/ 2016 ዓ/ም፦ በማዕከላዊ ትግራይ ዞን አበርጌሌ የጪላ ወረዳ እና በትግራይ ምስራቃዊ ዞን አጽቢ ወረዳ በተከሰተው ድርቅ ምክንያት የ190 ሰዎች ህይወት አለፈ። 

የአበርጌሌ የጪላ ወረዳ ጤና ኃላፊ ጌታቸው ታፈሰ ከአዲስ ስታንዳርድ ጋር ባደረጉት ቆይታ፣ በወረዳው የ83 ሰዎች ህይወት ማልፉን እና ተጨማሪ 297 ሰዎች በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ አስረድተዋል። በተጨማሪም በአሁኑ ወቅት ከ95,000 በላይ ሰዎች ለከፍተኛ አደጋ መጋለጣቸውን ጠቀሰው ሰብዓዊ ዕርዳታ በመጠባበቅ ላይ መሆናቸውንም አክለው ገልጸዋል።

የትግራይ ክልል አድጋ ስጋት መከላከል ኮሚሽን ኮሚሽነር ገብርህይወት ገ/እግዚአብሔር ለሚዲያ በሰጡት ማብራሪያ ደርቁ  12 ወረዳዎችን በሚያጠቃቅል በክልሉ ሶስት ዞኖች ማለትም በደቡብ፣ ደቡብ ምስራቅ እና ምስራቃዊ ትግራይ ዞኖችን አስከፊ ተጽዕኖ አድርሷል ብለዋል። በተጨማሪም በትግራይ ምዕራባዊ እና ማእከላዊ ዞኖች ውስጥ ያሉ የተወሰኑ አካባቢዎችም ከችግሩ ጋር እየታገሉ ነው ብለዋል፡፡

ገብርህይወት በክልሉ 19 ወረዳዎች ላይ አጠቃላይ የዳሰሳ ጥናት እየተካሄደ መሆኑን ጠቁመዋል። ከፌዴራል እና ከክልል የተውጣጡ ባለሙያዎችን ያቀፉት የጥናቱ ቡድኖች ሁኔታውን ምን ያህል አሳሳቢ እንደሆነ የአንድ ወር ግምገማ አድርጓል ነው ያሉት፡፡

ባሳለፍነው ሳምንት አዲስ ስታንዳርድ በአጽቢ ወረዳ ድርቅ ስላስከተለው አስክፊ ተጽእኖ መዘገቡ ይታወቃል።  የወረዳው ክላስተር ኃላፊ በርሄ ገብሬ ድርቁ እያድረስ ያላውን ተጽእኖ በመጠቆም ቢያንስ 107 ሰዎች ከረሃብ ጋር በተያያዘ ህይወታቸውን ያጡ ሲሆን ይህም በክልሉ ያለውን ቀውስ አሳሳቢነት ያመላክታል ብለዋል።

የትግራይ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ እያሱ አብርሃ እንዳሉት በክልሉ  በዋናነት በድርቅ ምክንያት ከአጠቃላይ 1 ነጥብ 3 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ውስጥ 660,000 ሄክታር የሚጠጋ ምርት ብቻ ነው የተሰበሰበው።አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button