ማህበራዊ ጉዳይዜና

ዜና፡ ኢትዮጵያ የአለም የስራ ድርጅት አባል ከሆነች 100 አመት ሞላት፣ ይህንንም በማስመልከት ሀገር አቀፍ ጉባኤ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ህዳር 21/2016 ዓ.ም፡- ኢትዮጵያ የዓለም የሥራ ድርጅት (ILO) አባል የሆነችበትን 100ኛ ዓመት በማስመልከት ሀገር አቀፍ ጉባዔ ሊካሄድ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ጉባኤው “ማህበራዊ ምክክርን እና የጎለበተ ምርታማነትን በመጠቀም ማህበራዊ ፍትህን ማላቅ” በሚል መሪ ሃሳብ ከኅዳር 24 እስከ 26 ቀን 2016 ዓ.ም በተለያዩ ኩነቶች ይካሄዳል ሲሉ ሚኒስትሯ ሙፈሪሃት ካሚል የጉባኤውን መካሄድ በማስመልከት በሰጡት መግለጫ መናገራቸውን አስታውቋል።

በጉባዔው ባለድርሻ አካላት በጋራ በመሆን ስኬቶች የሚገመገሙበት፣ ልምዶች የሚቀመሩበት፣ ለዘርፉ መጠናከር የሚያግዙ ምክረ ሀሳቦች የሚንሸራሸሩበት ይሆናል መባሉን ዘገባው ጠቁሟል።

የአለም ሥራ ድርጅት ሲቋቋም ኢትዮጵያ ከአፍሪካ በቀዳሚነት አባል መሆኗን ሚንስትሯ በማስታወስ ይህም ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የትብብር መድረኮች ላይ ሁሌም ግንባር ቀደም ሚና እንደምትጫወት ማሳያ ነው ማለታቸውን አካቷል።

በመስኩ ሥራቸውን በአግባቡ በመከወን ውጤታማ መሆን የቻሉ አካላትና ሠራተኞች ዕውቅና የሚሰጥበት መርሃ ግብር መዘጋጀቱን የጠቆመው ዘገባው በጉባዔው ከዓለም የሥራ ድርጅት ጋር ያለውን ትብብር እና ስኬቶች፣ የገጠሙ ተግዳሮቶች የሚፈታበት አቅጣጫ ላይ የጋራ ሀሳብ የሚያዝበት ነባሉን አመላክቷል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button