ዜናፖለቲካ

ዜና፡ በመንግስት እና በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት መካከል ቀጣይ ዙር የሰላም ድርድር እንዲጀመር በአሜሪካ የሚገኙ የኦሮሞ ሲቪክ ማህበራት ጠየቁ

አዲስ አበባ፣ ሀዳር 25/ 2016 ዓ/ም፦ በመንግስት እና በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት መካከል ቀጣይ ዙር የሰላም ድርድር እንዲጀመር በአሜሪካ የሚገኙ ሃያ ሶስት የኦሮሞ ሲቪክ ማህበራት ጠየቁ። የሲቪክ ማህበራቱ ለኢትዮጵያ መንግስት፣ ለኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት እና ለድርድሩ አምቻቾች በጻፉት ደብዳቤ በኦሮሚያ ክልል ለአምስት አመታት የሰዎችን ህይወት በመቅጥፍ ላይ ያልውን እና በርካታ ንብረትን ያወደመውን ግጭት ለማቆም ድርድር ተመራጭ ምንገድ መሆኑን እንደሚያምኑ ገልጸዋል።

በኦሮሚያ ክልል ያለውን ግጭት ለማቆም ታስቦ የፌዴራሉ መንግስትና የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት በታነዛኒያ ዳሬስላም ሲያካሄዱት የነበረው ሁለተኛው የሰላም ድርድር ያለ ውጤት በመጠናቀቁ ይታወቃል።

ሲቪክ ማህበራቱ በጻፉት ደብዳቤ ከውጭ አካላት ድጋፍ እና ግፊት ውጭ፣ ሁለቱም ወገኖች በረካታ ውድመት ያደርስውን ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት እና በክልሉ ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን ድፍረት የላቸውም ሲሉ ገልጸው የአለም አቀፉ ማህበረስብ ድርሻ ወስደው ግፊት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

“ሁላቱም ወገኖች ወደ መግባባቱ ተቃርበዋል ብለን እናምናለን፤ ስምምንት ላይ መድረስ ይቻላል ብለን እናምናለን። የፖለቲካ ትርፍን ወደ ጎን ትተው የኦሮሚያን ህዝብ ለማስጓዝ ቃል ገብተው ከተደራደሩ ገጭትን ከማቆም እና እርቅ ከማውረድ የሚያግዳቸው ነገር የለም” በለዋል። አክለውም “ሁለቱም ወገኖች ሊረዱት የሚገባው ነገር ወታደራዊ ድል በቀላሉ የማይገኝ እና በመጨረሻም ድርድር የማይቀር መሆኑን ነው” ብለዋል።

የኦሮሞ ሲቪክ ማህበራቱ በደብዳቤያቸው ሁለቱም ወገኖች በፍጥነት ወደ ድርድር እንዲመለሱ አሳስበዋል። “የኢትዮጵያ መንግስት በአንድ በኩል የሚቻለውን እንዲያደርግ እና ከኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ጋር መተማመን እና ሰላም ለመፍጠር የሚያስችሉ እርምጃዎች ላይ እንዲሰማራ እንጠይቃለን። በተጨማሪም መንግስት እና የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ግጭቱ ያስከተለውን ውድመት ተገንዝበው በመከባበር እና በመርህ ላይ የተመሰረተ ስምምነት እንዲያደርጉ እናሳስባለን።” ብለዋል። 

በተጨማሪም ማህበራቱ “ሌላው እንኳን መሆን ባይችል ለህዝቡ ሲባል በአስቸኳይ ተኩስ የማቆም ስምምነት እንዲያደርጉ ጥሪ እናቀረባለን” ሲሉ በመግለጫቸው ጠይቀዋል። አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button