ዜናፖለቲካ

ዜና፡ ኢሰመጉ ከመንግስት አካላት በሚደርስብኝ ተጽእኖ ስራየን በአግባቡ መስራት ተቸግሬያለሁ ሲል ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 28/2016 ዓ.ም፡- የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ጉባኤ ከመንግስት አካላት በሚደርስበት ልዩ ልዩ ተግዳሮቶች ምክንያት ስራውን በአግባቡ ለመስራት መቸገሩን አስታወቀ፤ ከመንግስት ተቋማት መረጃ አይሰጡኝም እየከለከሉኝ ነው ብሏል።

ኢሰመጉ ህዳር 27 ቀን 2016 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ የተቋቋመለትን አላማ ለማሳካት ይረዳው ዘንድ ከተለያዩ የመንግስት ተቋማት መረጃ እና ማስረጃዎችን እንዲሁም አንዳንድ የክትትል እና የምርመራ ስራዎችን ለመስራት የፈቃድ ጥያቄዎችን ለሚመለከታቸው የፌደራል እና የክልል መንግስታት ቢያቀርብ ከቅርብ ግዜያት ወዲህ ግን ተገቢ ምላኝ እያገኘ አለመሆኑን አስታውቋል።

ኢሰመጉ የሚያቀርባቸውን ደብዳቤዎች ለመቀበል ፈቃደኛ ያልሆኑ ተቋማት አሉ ሲል ተችቷል፣ በማሳያነትም መከላከያ ሚኒስቴር እና ሰላም ሚኒስቴር ለደብዳቤዎቹ ምላሽ አለመስጠታቸውን ገልጾ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጭራሽ ደብዳቤዎቼን ለመቀበል ፈቃደኛ አይደለም ብሏል።

በተጨማሪም ኢሰመጉ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር የሚገኙ የፌዳራል ማረሚያ ቤቶችንና ፖሊስ ጣቢያዎችን እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ ማረሚያ ቤቶችን እና ፖሊስ ጣቢያዎችን መጎብኘት ሳይችል መቅረቱን አመላክቷል። ይህም የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን አስመልክቶ ለሚሰሩ ስራዎች ተግዳሮት እንደሆነበት ጠቁሟል።

በተጨማሪም ኢሰመጉ በአዋሽ አርባ ኢ-መደበኛ በሆነ መልኩ የታሰሩ ጋዜጠኞች፣ የተፎካካሪ ፓርቲ አባላትና አመራሮች፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አባላት እና ሌሎችም የታሰሩ ግለሰቦችን አስመልክቶ እና እየተፈጸመባቸው ያለውን ከፍተኛ የሆነ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን ክትትል እና ምርመራ ለማድረግ ተደጋጋሚ የፈቃድ ጥያቄዎችን ያቀረበ ቢሆንም ምንም አይነት ክትትልም ሆነ ምርመራ ለማድረግ መከልከሉን አስታውቋል።

በፌደራል እና በክልል የሚገኙ የመንግስት ባለድሻ አካላት መረጃን የማጋራት ኃላፊነት ያለባቸው በመሆኑ መረጃን በማጋራት ለሰብዓዊ መብት መከበር የድርሻቸውን እንዲወጡ ሲል ኢሰመጉ ጥሪ አቅርቧል።

በአዋሽ አርባ ታስረው የሚገኙ ሰዎችን መንግሰት በአስቸኳይ መደበኛ ወደሆነ ፖሊስ ጣቢያ ወይም ማረሚያ ቤት እንዲያዘዋውር እንዲሁም ይህንን ኢመደበኛ ማቆያ ቦታ ለመጎብኘት ኢሰመጉ ለሚያቀርባቸው ጥያቄዎች ተገቢውን መልስ እንዲሰጠው አሳስቧል። አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button