ርዕሰ አንቀፅ
በመታየት ላይ ያለ

ርዕስ አንቀጽ: ቅሬታዎች እያሉ ኢትዮጵያ በሽግግር ፍትህን ስራ ላይ የማዋል ሂደቷን መቀጠሏ ለእውነተኛ ፍትህ እና እርቅ ስጋት እየጣለ ነው፤ ክለሳ እና ማስተካከያ እንዲደረግ ጥሪ እናቀርባለን!

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9/2016 ዓ.ም፡- በፖለቲካ ጥቃት ሰለባ የሆኑ ዜጎቿ ፍትህ እንዲያገኙ፣ ተጠያቂነት እና እርቅ እንዲሰፍን ለማስቻል ኢትዮጵያ ከቅርብ ግዜያት ወዲህ ጥረት ስታደርግበት የነበረው የሽግግር ፍትህ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ደርሷል። ከሳምንታት በፊት የሚኒስትሮች ምክር ቤት ብሔራዊ የሽግግር ፍትህ ፖሊሲን አጽድቋል፣ ይህም በሽግግር ፍትህ ሀገሪቱ ወደ ፊት ለመጓዝ ለምታደርገው ጥረት ወሳኝ እርምጃ ተደርጎ ተወስዷል።

ይሁን እንጂ ፖሊሲውን ለማስጸደቅ የተሄደበት ጉዞ አሳሳቢ በሆኑ ስጋቶች የተሞላ ነበር፤ የዘርፉ ባለሞያች የይምሰል አካሄድ ሲሉ የፈረጁት ሲሆን ለዚህም የሚያቀርቡት ምክንያት በዋናነት እውነተኛ ፍትህ እና ተጠያቂነት ከማስፈን ይልቅ ከተጠያቂነት ለመሸሺያ መንግድ ተብሎ የተቀረጸ ነው የሚል ነው።

ቅሬታ መፈጠር የጀመረው በመጋቢት 2023 ዓ.ም የፍትህ ሚኒስቴር ለሽግግር የፍትህ ፖሊሲን እንደ አማራጭ ሰነድ ይፋ ባደረገበት ወቅት ነበር። በመቀጠልም በሚኒስቴሩ የተመረጡ የባለሙያዎች ቡድን ተቋቋመ እና ለፖሊሲ ቀረጻ ግብአት ለማሰባሰብ በሚል ሰፊ ህዝባዊ ምክክር ማካሄድ ጀመረ።

አለመሳካቱ ጽንሰ ሀሳቡን ከማሳበቁም በላይ ከመሠረታዊ መርሆቹ አንዱ የሆነውን ለተጎጂዎች ፍላጎት ቅድሚያ መስጠት የሚለውን የሚሸረሽር ነው።

ከመጀመሪያው ጀምሮ በሽግግር ፍትህ ሂደቱ የፍትህ ሚኒስቴር ዋነኛና ወሳኝ አካል ሁኖ መሳተፉ፣ ከዚያም ፖሊሲውን የሚያረቁ የባለሞያዎች ቡድኑን እራሱ መምረጡ ጥያቄ እንዲነሳበት አድርጓል። ይህም የበርካታ የሀገሪቱ ተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች በዚያኑ አመት መጋቢት ወር የምክክር ስብሰባ እንዲያካሂዱ እና ሂደቱንም እንዲቃወሙ አድርጓቸዋል።

ፓርቲዎቹ ለተቃውሟቸው በዋናነት ያለሱትም አካታችነቱን እና ተአማኒነቱን ሲሆን በወቅቱ የሰነዘሩት አስተያየትም መንግስት የሽግግር ፍትህ ማዕቀፉን ለፖለቲካ ፍጆታ እና አለም አቀፍ ቅቡልነት ማግኛ መጠቀሚያ ከማድረግ ይልቅ ለሰላም እና ዕርቅ ቅድሚያ እንዲሰጥ የሚጠይቅ ነበር።

በርከታ ስጋቶች ቢቀርቡም የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሰነዱን አጽድቆታል፣ ይህም አሳማኝ በሆኑ ምክንያቶች የሽግግር ፍትሁ ተቀባይነት እንዳይኖረውና ውድቅ የመሆኑን እድል ከፍ አድርጎታል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

በአማራ እና ኦሮምያ ክልሎች ግጭቶች በመካሄድ ላይ እያሉ፣ ከፖለቲካዊ ግጭት ሊያሸጋግር የሚችል ግልጽ አካሄድ ሳይኖር ለመተግበር መሞከር አካሄዱ የሽግግር ፍትህ ዋነኛ ባህሪን የሚቃረን ለመሆኑ ፍንትው ያለ እውነታ ነው።

በሰብአዊ መብት ጥሰቶች እና ወንጀሎች የታጀቡ ግጭቶች በመካሄድ ላይ እያሉ ፖሊሲውን ለመተግበር መጣደፍ የሂደቱን ውጤታማነት ጥያቄ ውስጥ ከመክተቱ ባለፈ የሚመጣው ውጤት ቅቡልነት እንዳይኖረው የሚያደርግ ነው።

አለመሳካቱ ጽንሰ ሀሳቡን ከማሳበቁም በላይ ከመሠረታዊ መርሆቹ አንዱ የሆነውን የተጎጂዎችን ፍላጎት ቅድሚያ መስጠት የሚለውን የሚሸረሽር ነው።

ሌላኛው የሽግግር ፍትህ ሂደቱን የሚያሳብቀው ጉዳይ ከፍተኛ ወንጀሎችን ፈጽሟል ተብሎ የሚወነጀለው መንግስት ፖሊሲውን በማርቀቅ ላይ ብቻ ሳይሆን በቀጣይ ትግበራው ላይ የሚኖረው ከፍተኛ የተሳትፎ እጅ ነው።

ሌላኛው በመነሳት ላይ ያለው ስጋት በትግራይ ክልል የሚገኙ ተጎጂዎችን አለማካተቱ ነው፤ አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ባለሞያዎች ቡድን ኮሚሽንን ጨምሮ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት እና ታላላቅ የአለማችን የሰብአዊ መብት ተሟጋች ተቋማት በትግራዩ የሁለት አመት ጦርነት ወቅት የዘር ማጽዳት፣ የጦር ወንጀል እና በሰብአዊነት ላይ የተፈጸመ ወንጀሎች መፈጸማቸውን የሚያሳዩ በማስረጃ አስደግፈው ሪፖርቶች ማቅረባቸው ይታወቃል።

በተመሳሳይ የሚቀርበው ሌላኛው ስጋት ደግሞ የፖሊሲ ቀረጻ እየተካሄደ በነበረበት ወቅት በኦሮምያ እና በአማራ ክልሎች ግጭቶች መካሄዳቸው ነው።

ሌላኛው የሽግግር ፍትህ ሂደቱን የሚያሳብቀው ጉዳይ ከፍተኛ ወንጀሎችን ፈጽሟል ተብሎ የሚወነጀለው መንግስት ፖሊሲውን በማርቀቅ ላይ ብቻ ሳይሆን በቀጣይ ትግበራው ላይ የሚኖረው ከፍተኛ የተሳትፎ እጅ ነው።

ይህ የተንሰራፋው የመንግስት ተሳትፎ ሂደቱን ውጤታማ እንዳይሆን ከማድረጉም ባሻገር በህዝብ እና በሌሎች ባለድርሻ አካላት መካከል አለመተማመን እንዳይፈጠር ያደርጋል።

በፖሊሲው ድንጋጌ መሰረት ምርመራው እና ክሱ አሁን ባለው የፍርድ ቤት ስርዓት ውስጥ ልዩ አቃቤ ህግ እና ልዩ የፍርድ ችሎት ተቋቁመው እንዲታይ ያደርጋል።

ሆኖም የኢትዮጵያ መንግስት ገለልተኛ ምርመራዎችን ከመጥላት ጀምሮ ያለው ታሪክ እንደሚያሳየው ተጎጂዎች የተሳካ የሽግግር ፍትህ ሂደት ያገኛሉ ብሎ መጠበቅ የማይመስል ነገር ነው።

ምንም እንኳን ሂደቱ መንግስት በተፈለገው መንገድ ቢካሄድም ትልቅ እንቅፋት አለ፤ ወንጀል ፈጻሚዎችን ድርጊት በሀገር ውስጥ ባለሞያዎች የማየት የአቅም ገደብ እና የውጭ ሀገር ወንጀል ፈጻሚዎችን ለፍርድ ማቅረብ የሚሉት፤ በተለይም በትግራይ ክልል ንጹሃን ላይ የጦር ወንጀል እና በሰብአዊነት ላይ የተፈጸመ ወንጀል የሰሩትን የኤርትራ ሀይሎችን ለፍርድ ማቅረብ።

ከላይ ከተጠቀሱት ዋነኛ ስጋቶች በተጨማሪ ፖሊሲው ሆን ተብሎ በሚያወሳስቡ ጉዳዮች የተሞላ ነው፤ ለምሳሌ የብሔር ብሔረሰቦች ህገመንግስት ተግባራዊ ከተደረገበት ከ1987 ዓ.ም ጀምሮ በተፈጸሙ ሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ጀምሮ የሚል የጊዜ ወሰን እንዲካተት መደረጉ ሊጠቀስ የሚችል ነው።

ባለሞያተኞች በመከራከሪያነት እንደሚያቀርቡት አለም በአንድ ድምጽ በኮነናቸው እና ለፖሊሲው መርቀቅ ከመነሻው ምክንያት የሆኑትን እንዲሁም በቂ ማስረጃ ሊቀርብባቸው የሚችሉ እና ባለፉት አራት አመታት የተፈጸሙ ወንጀሎችን በመሸፋፈን ተጠያቂነት እንዳይሰፍን ከማድረጉ ባለፈ የዕርቅ ሂደቱን የሚያደናቅፍ ነው።

ከወንጀለኝነት ጋር በተያያዘ አሻሚ ሁነው እንዲካተት የተደረጉት የህግ ቃላት ማለትም የወንጀል ተጠያቂነት የሚካሄደው “በከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች” ብቻ ነው የሚለውን ጨምሮ በወንጀሉ “ከፍተኛ ተሳትፎ” የነበራቸውን ተጠያቂ እንደሚያደርግ መገለጹ ተጎጂዎች በሂደቱ ቅንጣት ታክል እምነት እንዳይኖራቸው የሚያደርግ ነው።

በኢትዮጵያ ውስጥ ተጠያቂነት፣ ፍትህ እና የፖለቲካ መረጋጋት ለማስፈን ያግዛል በሚል ለሂደቱ ድጋፍ ሲያደርጉ የነበሩ አለም አቀፍ አጋሮች አቋማቸውን እንደገና መፈተሽ ይኖርባቸዋል። ያልተሳኩ የሽግግር ፍትህ ሂደቶች ወደ እውነተኛው የሽግግር ፍትህ ለሚደረጉ ጉዞዎች እንቅፋት እንደሚሆኑ መገንዘብ ያስፈልጋል፤

መንግስት በሽግግር ፍትህ ዙሪያ የሚቀርቡ ስጋቶችን በበቂ ሁኔታ ሳይቀረፉ የፖሊሲ ትግበራውን  ለማስቀጠል ቁርጠኛ መሆኑ ሀገሪቱ እውነተኛ ተጠያቂነት፣ ፍትህ እና እርቅ ለማድረግ የሚኖራትን ተስፋ የሚጎዳ ነው።

በኢትዮጵያ ውስጥ ተጠያቂነት፣ ፍትህ እና የፖለቲካ መረጋጋት ለማስፈን ያግዛል በሚል ለሂደቱ ድጋፍ ሲያደርጉ የነበሩ አለም አቀፍ አጋሮች አቋማቸውን እንደገና መፈተሽ ይኖርባቸዋል።

ያልተሳኩ የሽግግር ፍትህ ሂደቶች ወደ እውነተኛው የሽግግር ፍትህ ለሚደረጉ ጉዞዎች እንቅፋት እንደሚሆኑ መገንዘብ ያስፈልጋል፤ በተጨማሪም የግጭት አዙሪቱን በማጦዝ ጭካኔ የተሞላበት እና መፍትሔ አልባ እንዲሆን ያደርገዋል።

አዲስ ስታንዳርድ ሁሉም ተሳታፊዎች ቆም ብለው እንዲያስቡ፣ ሀሳባቸውን እንዲያንጸባርቁ እና አካሄዳቸውን እንዲያጤኑ ጥሪ ያቀርባል! አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button