ዜናርዕሰ አንቀፅ
በመታየት ላይ ያለ

ርዕስ አንቀጽ: በሀገሪቱ የሚንቀሳቃሱ ዋነኛ የታጠቁ እና ያልታጠቁ ተቃዋሚ ቡድኖችን ሳያሳትፍ የሚካሄድ ሀገራዊ ምክክር ውጤት አልባ ከመሆን አይዘልም

አዲስ አበባያካቲት 22/ 2016 ዓ/ም፡ – ለኢትዮጵያ ውስብስብ የፖለቲካ ቀውስ መፍትሔ ያስገኛል እንዲሁም ሀገራዊ መጻኢ ሁኔታ ላይ መግባባት ለመፍጠር ያግዛል የተባለለት ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ያካሄደውን ቅድመ ዝግጅት ስራዎች በማጠናቀቅ ላይ ነው። በመሆኑ በቅርብ ወራት ውስጥ ሀገራዊ ምክክሩ ይጀመራል ተብሎም ይጠበቃል።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ታህሳስ 20/2014 ዓ.ም የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን መቋቋም የተመለከተውን አዋጅ ቁጥር 1265/2014 ማጽደቁ ይታወሳል፤ ከዚያም ምክር ቤቱ የካቲት 14 ቀን 2014 ዓ.ም 11 ኮሚሽነሮችን ሾሟል።

ከምስረታው ጀምሮ ኮሚሽኑ ከሀገሪቱ ዋና ዋና የፖለቲካ ፓርቲዎች ጀምሮ እስከ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት (በምርጫ ቦርድ በህጋዊነት የተመዘገቡ 53 ፖለቲካ ፓርቲዎችን በጋራ ያቀፈው) ድረስ ውግዘት እና ትችት አስተናግዷል።

በወቅቱ ኮሚሽኑ በተለያዩ ምክንያቶች ሂደቱን በግዜያዊነት እንዲያቆም ተጠይቆም ነበር፤ በምክንያትነት ከቀረቡት መካከልም ባለድርሻ አካላት የተሟላ ተሳትፎ ለማድረግ እንዲቻል፣ ሊወስዳቸው ስለሚገባ እርምጃዎች ማጤን እንዲችል እና አካሄዱ ግልጽነት የተከተለ እንዲሆን ለማስቻል የሚሉትይገኙበታል።

በዚያን ግዜ በየወሩ በሚታተመው አዲስ ስታንዳርድ መፅሔት የግንቦት 2014 ዓ.ም ዕትም ርዕስ አንቀጽ ላይ ለመሞገት እንደተሞከረው ገዢው ፓርቲ ብቻውን በመቆጣጠር የኮሚሽንኑ ምስረታ ለማስጸደቅ እና ኮሚሽነሮችን ለማሾም መሞከሩ በሁለት ምክንያቶች ትልቅ ፈተና ይገጥመዋል በሚል ተቀምጦ ነበር፤ ወቅቱን ያልጠበቀ መሆኑ እና የቅቡልነት ማጣት።

ወቅቱን የጠበቀ አለመሆኑ: የሀገሪቱን የፖለቲካ ሽግግር ውጥረት መፍትሔ ለማበጀት እንዲሁም ሀገራዊ ምክክር ለማካሄድ ወሳኝ የነበረው ባቡር ሃዲዱን የሳተው በ2010 ዓ.ም ነበር። በወቅቱ በፌደራል መንግስት እና በኦሮምያ ክልል በሚንቀሳቀሱ ታጣቂ ሀይሎች (የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት) መካከል በጦር መሳሪያ የተደረገፈ የትጥቅ ትግል ተጀምሯል። ከዚያን በኋላ ኢትዮጵያ በዋነኝነት በመጥፎ የፖለቲካ የተቃኘ የበርካታ ግጭቶች መናሀሪያ ሁና ነበር። ይህ ሁኔታ መጨረሻው በትግራይ የተጀመረው የእርስ በርስ ጦርነት ሆነ። በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምዕራብ እስከ ምስራቅ  ወታደራዊ ግጭት የተንሰራፋበት ቀጠና ሁኗል። በአፋጣኝ የሚያስፈልገን መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑትን ያሳተፈ የተንሰራፋውን ጥላቻ ማስቆም የሚያስችል የተቀናጀ ፍኖተ ካርታ ነው። ከዚያም የተኩስ ማቆም ስምምነት በመፈጸም ሀቀኛ የፖለቲካ ድርድር ማካሄድ።

ቅቡልነት: ምርጥ የአለማችን ተሞክሮዎች እንደሚያሳዩት የተሳካ ብሔራዊ ምክክር የሚሳካው በገለልተኛ አካላት ሲመራ ነው። ምክክሩ ሊፈታቸው ከሚገቡ ችግሮች መካከል የሆኑ አንገብጋቢ ሁኔታዎችን የፈጠረው አካል ገዢው ፓርቲ እራሱ ሙሉ በሙሉ የተቆጠጠረው እና በኮሚሽነርነት ትልቅ ሚና የሚጫወቱትን ሰዎች ጭምር በመምረጥ የተካሄደ ሀገራዊ ምክክር ስለመኖሩ አለማችን አራሷ መሳያ የምታቀርብ አይመስልም።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

ምንም እንኳ ግልጽ ጥሰት ቢፈጽምም ገዢው ፓርቲ በተደጋጋሚ በተቃዋሚ ፓርቲዎች እና የሚመለከታቸው አካላት ሲቀርብ የነበረው ጥያቄ በአዋጁ አጸዳደቅ እና በኮሚነር አሻሻም ሂደቱ ግልጽነት አካታች ይሁን የሚል ነበር። ማንም ፓርቲ ሂደቱን ገዢው ፓርቲ ብቻውን ተቆጣጠረው ብሎ አልቀበልም ያለ አልነበረም፣ ምንም እንኳ ይህን ማለት ህጋዊ ቢሆንም።

ከሁለት አመታት በኋላ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ከትግራይ እና አማራ ክልሎች ውጭ የተሳታፊዎችን ልየታ አገባድጃለሁ እያለ እና ወደ አጀንዳ ማሰባሰብ ተሸጋግሬያለሁ ሲል እየገለጸ ባለበት ወቅት እንኳን እነዚህን አንገብጋቢ ጉዳዮች ግምት ውስጥ ማስገባት አልፈለገም።

ምንም እንኳ በጥቅምት ወር 2014 ዓ.ም በፕሪቶርያው ስምምነት የትግራይ ጦርነት ያቆመ ቢሆንም ሌላ ግጭት በአማራ ክልል በመካሄድ ላይ ይገኛል። በኦሮምያ ክልል በመካሄድ ላይ ያለውን ግጭት በሰላማዊ ድርድር ለመቋጨት የተደረገው ሙከራም አልተሳካም፤ ግጭቱ እና ውጊያው አሁንም ከመቸውም ግዜ በላይ ተባብሶ ቀጥሏል።

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ከመንግስት ጋር በመፋለም ላይ ያሉ ታጣቂ ሀይሎችንም በምክክሩ ለማሳተፍ ፍላጎት እንዳለው ከመግለጽ ባለፈ ምንም ተግባራዊ እንቅስቃሴ ሲያደርግ አልታየም። እንዴት እንደሚሳተፉም ያስቀመጠው ምንም ፍኖተ ካርታ አላቀረበም።

በሀገር ውስጥ ከሚታተም ጋዜጣ ጋር ቃለምልልስ ያካሄዱ አንድ ኮሚሽነር እንደገለጹት ከሆነ ኮሚሽኑ ታጣቂዎቹ ከመንግስት ጋር እየተዋጉም ቢሆን በምክክሩ የሚሳተፉበት የሆነ መንገድ ይኖር ይሆናል የሚል ተስፋ ብቻ ነው የያዘው።

በተጨማሪም በሀገሪቱ ከሚገኙ 63 ተቃዋሚዎች ውስጥ ከ40 በላይ የሚሆኑት ከኮሚሽኑ ጋር እየሰሩ መሆናቸውን በመግለጽ ኮሚሽኑ ቅቡልነቱን በተሳካ ሁኔታ መመለሱን ይናገራል።

ይሁን እንጂ ለምሳሌ፤ በኦሮሚያ ክልል፤ ትልቅ ተጽዕኖ ያላቸው ታወቂዎቹ ሁለት ፓርቲዎች ማለትም የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ(ኦፌኮ) እና የኦሮሞ ነጻነት ግንባር(ኦነግ) እስካሁን በሂደቱ ላይ ለመሳተፍ ፍቃደኛ ባለመሆነቸው የኮሚሽኑ ቅቡልነት ላይ ጥርጣሬ አስከትሏል።

እነዚህ ሁለት ፓርቲዎች እና ታጣቂውን የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት (ኦነሰ) ቡድን ያላካተተ አገራዊ ምክክር ውጤት በኦሮሚያ ክልል ብቻ ሳይሆን በሀገር አቀፍ ደረጃም ቢሆን ብዙም ተፅዕኖ እንደሌለው ግልጽ ነው። በተጨማሪም በአማራ ክልል ከመንግስት ጋር በመዋጋት ላይ የሚገኙት ፋኖ ታጣቂዎች በተሳካ ሁኔታ አለመካተታቸው አጠቃላይ ሂደቱን ውጤት አልባ ያደርገዋል። ትግራይን በተመለከተ፤ ከክልሉ አንድም ተወካይ በሌለበት በፓርላማ የተቋቋመው ኮሚሽኑ፤ ባለስልጣናቱ ተሳትፎአቸውን በቃል ብቻ ነው ያረጋገጡለት።

እንድ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፤ “አጋራዊ ምክክሩ ስምምነት ላይ ለመድረስና ስምምነቱን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችለው ዋነኛ ተጽዕኖ፤ ከሌላው ህብረተሰብ ጋር ሲነፃፀር ያልተመጣጠነ የፖለቲካ፣ የማኅበራዊና የኢኮኖሚ ሥልጣን ያላቸው የአገሪቱ ልሂቃን አመለካከትና ባህሪ ነው”።

ይህ ማለት፤ ያለ ሊህቃኑ ተሳትፎ እና የኮሚሽነሮች ቁርጠኝነት እንዲሁም ኮሚሽኑ ያከናወነው የሚያስመሰግን የታሳታፊዎች ልየታ ስራ እና አጀንዳ የማሰባሰብ ጥረት፤ የሂደቱ ውጤታማነት ያን ያህል አይሆንም።

አሁንም ቢሆን ላይረፍድ ይችላል። በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች ጊዜያዊም ቢሆን የተኩስ አቁም እንዲፈፀም የሚያደርግ አሰራር ማዘጋጀት እና የታጠቁ ቡድኖችን ብቻ ሳይሆን ቁልፍ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችን እና ሌሎች ወሳኝ ባለድርሻ አካላትን ማካተት ሂደቱን ወደ ተግባር ለማምጣት እና የታሰቡትን ዓላማዎች ለማሳካት አስፈላጊ ነው። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button