ርዕሰ አንቀፅ
በመታየት ላይ ያለ

ርዕሰ አንቀጽ፡ በኢትዮጵያ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በረሃብ ከሞቱ በኋላ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች በአስከፊ አደጋ ውስጥ ናቸው፤ መካዱ ይቁምና ከመርፈዱ በፊት ብሔራዊ አደጋ መሆኑ ይታወጅ!

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 19/2016 ዓ/ም፡ በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች በተለይም በአማራ እና ትግራይ ክልሎች ለተከታታይ አመታት በተከሰተው ድርቅ እና ጦርነት ምክንያት የመኀር ምርት በመቋረጡ በመቶዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች በረሃብ መሞታቸው የማይካድ ሀቅ ነው።  

ባለፉት አራት ዓመታት ውስጥ፣ በህንድ ውቅያኖስ ዲፖሌ እና የላኒና አየር ጸባይ ሁኔታዎች ምክንያት በአማካኝ ዝቅተኛ የዝናብ መጠን በመከሰቱ ኢትዮጵያ በአስከፊ ድርቅ ውስጥ ትገኛለች።  የማስጠንቀቂያ ምልክቶችም ነበሩ።

በትግራይ ክልል በአራት ወረዳዎች በታህሳስ ወር ብቻ 25 ህጻናትን ጨምሮ ከ400 በላይ ሰዎች በረሃብ ምክንያት መሞታቸውን የክልሉ ባለስልጣናት በቅርቡ አምነዋል። ከዚህ ውስጥ ግማሽ የሚሆኑት ሰዎች የሞቱት፣ ቀድሞውኑ የተከሰተው ጦርነት እና ከበባ ባስከተለው ተፅዕኖ ምክንያት እየተሰቃየ የነበረው ህዝብ፤ በከፍተኛ የዝናብ እጥረት ለከፋ ችግር በተዳረገበት በማዕከላዊ ዞን አበርጌሌ የጭላ እና በምስራቅ ዞን አፅቢ ወረዳዎች ላይ ነው።

በደቡብ፣ ደቡብ ምስራቅ እና ምስራቅ ትግራይ ዞኖች ቢያንስ 132,000 ሄክታር የእርሻ መሬት ላይ ከባድ ድርቅ በመከሰቱ ለመጪው አመት የመኀር ምርት አደጋ ጋርጧል። በአሁኑ ወቅት በክልሉ በአምስት ዞኖች ውስጥ  ባሉ 32 ወረዳዎች ከሁለት ሚሊዮን በላይ ሰዎች ከፍተኛ የምግብ እጥረት እያጋጠማቸው ነው፤ ይህም የክልሉ ባለሥልጣናት ሊከሰት ለሚችለው የሰብአዊ ቀውስ ምላሽ ለመስጠት “አፋጣኝ ምላሽ ለትግራይ” የተሰኘ ግብረ ሃይል እንዲያቋቁሙ አድርጓቸዋል።

በተመሳሳይ መልኩ በአማራ ክልል በተለይ በዋግ ኀምራ ብሔረሰብ አስተዳደር እና ሰሜን ጎንደር ዞኖች ውስጥ የተከሰተው አስከፊ ድርቅ፤ እየተካሄደ ካለው ግጭት ጋር ተደምሮ በአካባቢዎቹ ህዝብ ላይ አስከፊ ተጽእኖ እያሳደረ ነው። በህዳር ወር በሁለቱ ዞኖች ከ20 ባላይ ሰዎች በረሃብ መሞታቸው እና ከ85 ሺህ በላይ እንስሳት በድርቅ መሞታቸው ተገልጿል።  በክልሉ በተከሰተው ግጭት ሳቢያ ህይወት የማዳን ሰብዓዊ ዕርዳታ ሰራዎች እየተደናቀፉ ሲሆን ድርቅና የሰብል መጥፋት በክልሉ በ43 ወረዳዎች የሚኖሩ ወደ አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ ዜጎችን ለረሃብ ዳርጓቸዋል።

በደቡብ እና ደቡብምስራቅ ኢትዮጵያ በተለይ በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን እና በሶማሌ ክልል ሊበን፣ አፍዴር እና ዳዋ ዞኖች ተከስቶ ከነበረው ከባድ ድርቅ የማገገሙ ሂደት የተንቀራፈፈ በመሆኑ የረሃብ አደጋ ሊኖር ይችላል የሚል ስጋት አለ።

ፊውስ ኔት (FEWS NET) የተሰኘ ተቋም በቀርቡ ባወጣው ሪፖርት መሰረት በዞኖቹ ተፈናቅለው የሚገኙ እና መሰረታዊ ፍላጎታቸውን ማሟላት ያልቻሉ እጅግ በርካታ ኢትዮጵያውያን ምግብ ለማግኘት እጅግ እየተቸገሩ ነው። ከጎርፍ አደጋ ጋር በተያያዘ የሚከሰት ተጨማሪ መፈናቀል እና ተጨማሪ የንብረት መጥፋት ሊከሰት የሚችልበት እድል ከፍተኛ በመሆኑ፣ ፊውስ ኔት በአካባቢዎቹ ረሃብ የመከሰት እድል መኖሩን ገልጿል። 

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

…የተሰጠው ምላሽም ሆነ ፌዴራል መንግስት ባለስልጣናት ለችግሩ የሰጡት ትኩረት፣ ባለፉት ሁለት ወራት ውስጥ በተግባር ከሚታየው ከፍተኛ የምግብ እጦት ጋር የሚጣጣም አይመስልም።

ተቋሙ ድርቅ የተከሰተባቸው የትግራይ ክልል፣ በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ ሶማሌ እና ኦሮሚያ ከልሎች እና ስሜን ምስራቅ አማራ ክልል አካባቢዎችን “ለከፈተኛ ረሃብ አደጋ” የተጋለጡ (‘Emergency’ (IPC phase 4) ሲል መድቧቸዋል። ይህም ከታሰበው በላይ ከባድ አደጋ ሊያስከትል ይችላሉ በሏል።  በዚህም ምክንያት ከመኀር ምርት እና ከአንሰሳት የሚገኘው ገቢ ከሚጠበቀው በታች ከሆነ በ2024 መጀመሪያ ላይ “እጅግ አሳሳቢ ረሃብ አደጋ” Catastrophe (IPC Phase 5) ይከሰታል ሲል አስጠንቅቋል። 

ስድስተኛው ደረጃ ማለትም አይፒሲ ፌዝ ስድስት (IPC Phase 6) እንድመይኖርም ነው የገልጸው። 

ነገር ግን፣ የተሰጠው ምላሽም ሆነ ፌዴራል መንግስት ባለስልጣናት ለችግሩ የሰጡት ትኩረት፣ ባለፉት ሁለት ወራት ውስጥ በተግባር ከሚታየው ከፍተኛ የምግብ እጦት ጋር የሚጣጣም አይመስልም።

ይባስኑ የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ሽፈራው ተክለማርያም (ዶ/ር)፣ ድርቁ ወደ ረሃብ መቀየሩን  እና በረሃብ ሰዎች መሞታቸውን የሚገልጹ መረጃዎችን በማሠራጨት ላይ ያሉ ወገኖች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳስበዋል። ኮሚሽነሩ ከፋና በሮድካስቲን ኮሮፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ “ የተከሰተው ድርቅ ወደ ረሃብ ተቀይሯል የሚሉ መረጃዎች ሌላ ዓላማ ይዘው የሚንቀሳቀሱ አካላት የሚያዘዋውሯቸው ናቸው” በለዋል። 

ይህን ጥሪ ያስተላለፍነው በአገሪቱ በረካታ አካባቢዎች የተከሰተው ድርቅ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ አባወራዎችን ህይውት አደጋ ላይ መጣሉን እና በሚሊዮን የሚቆጠሩ አንስሳትን መግደሉን ሪፖርተሮቻችን በስፍራዎቹ በመገኘት ማጋለጣቸውን ተከትሎ ነው። 

ኮሚሽነር ሽፈራው ተክለማርያም (ዶ/ር) ድርቁ በተከሰተባቸው በአማራ ክልል ባሉ ሥምንት ዞኖች፣ በአፋር ክልል ባሉ ሦስት ዞኖችና በትግራይ ክልል በሚገኙ ሦስት ዞኖች፣ ከአጋር ተራድዖ ድርጅቶች የተገኘውን 4.2 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ጨምሮ በአጠቃላይ የ15 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ለሰብዓዊነት ድጋፍ እየተዳረሰ መሆኑን ገልጸዋል።

በተጨማሪም በተመሳሳይ ቃለ መጠይቃቸው ኮሚሽነሩ የፀጥታ ችግሮች ምክንያት በአንዳንድ አካባቢዎች ሰብዓዊ ዕርዳታ ለማድረስ አስቸጋሪ መሆኑን ቢገልጹም ነገር ግን ይችግሩን አስከፊነት ወይም ከሚከሰተው አደጋ ጋር የሚጣጣም እርምጃዎችን ሳይጠቁሙ ቀርተዋል።

በየካቲት ወር 2015 ይህ ዕትም ተገቢውን ምላሽ እንዲሰጥ መንግስት ድርቁ ብሔራዊ አደጋ መሆኑን እንዲያውጅ አሳስቧል። ይህን ጥሪ ያስተላለፍነው በአገሪቱ በረካታ አካባቢዎች የተከሰተው ድርቅ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ አባወራዎችን ህይውት አደጋ ላይ መጣሉን እና በሚሊዮን የሚቆጠሩ አንስሳትን መግደሉን ሪፖርተሮቻችን በስፍራዎቹ በመገኘት ማጋለጣቸውን ተከትሎ ነው። ከ20 ወራት በኋላ፣ የአንድ መቶ ሰዎች ህይወት ሲጠፋም፤ መንግስት አደጋነቱን ከማውጅ እና ብሔራዊ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ የችግሩን አስካፊነት እየካደ ነው።

በ1977 ዓ/ም በኢትዮጵያ በተከሰተው ረሃብ፣ አንድ ሚሊዮን የሚሆኑ ዜጎች በረሃብ ህይወታቸው ሲያልፍ፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ደግሞ ተጎጂ ሆነዋል። ከዛ አስካፊ ክስተት በኋላ በቅርቡ በአማራ እና በትግራይ ክልሎች በረሃብ ምክንያት የተከሰተው ሞት በክልሎቹ ባለስልጣናት ይፋ ሲደረግ የመጀመሪያው መሆኑ መታወቅ አላበት።

ሚሊዮኖች በሞት አፋፍ ላይ ናቸው። ባለሥልጣናቱ በአጥራሩ ላይ መከራከራቸውን በማቆም፣ ከመርፈዱ በፊት ተገቢውን ምላሽ ለማስተባበር ቀውሱ ብሔራዊ አደጋ መሆኑን ማወጅ አለባቸው። 

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር “አስቸኳይ ጊዜ ምላሽ ኮሚቴ” ከሟቋቋሙ በተጨማሪ ለአስቸኳይ ህይወት አድን የሚውል 50 ሚሊዮን ብር መድቧል። በተጨማሪም ጊዚያዊ አስተዳደሩ የተመደበው ገንዘብ በቂ አለመሆኑን በመግለጽ፤ የክልሉ ተወላጅ ባለሃብቶች፣ የትግራይ ዳያስፓራዎች እና ጉዳዩ የሚያሳስባቸው ባለድርሻ አካላት ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል። ይህ የሚደነቅ ተግባር ቢሆንም፣ የተቀናጀ ምላሽ ዘዴን ለማመቻቸት እና ለማፋጠን ከፌዴራል መንግስት ጋር የተቀናጀ ጥረት ማድረግ ያስፈልጋል።

ለአብነት ያህል በአማራ ክልል ዋግ ኽምራ ዞን መረዳት ካለበት የህብረተሰብ ክፍል መካከል 42 ከመቶ የሚሆኑት ብቻ የአንድ ዙር የምግብ እርዳታ ማግኘታቸውን የአካባቢው ባለስጣናት አስታውቀዋል፡፡ እንደዚህ ያሉ አሳዛኝ ሁኔታዎች አየተፈጥሩ፣ ይህ እንደ መደበኛ ምላሽ ሊወሰድ አይችልም።

የቀውሱን አስከፊነት በትክክል አለመረዳት ወይም በረሃብ ምክንያት የተከሰተ የረዳት አልባ ንጹሃን  ዜጎችን ሞት አለመቀበል ለአደጋው የሚሰጠውን ምላሽ በእጅጉ ይጎዳል። ሚሊዮኖች በሞት አፋፍ ላይ ናቸው። ባለሥልጣናቱ በአጥራሩ ላይ መከራከራቸውን በማቆም፣ ከመርፈዱ በፊት ተገቢውን ምላሽ ለማስተባበር ቀውሱ ብሔራዊ አደጋ መሆኑን ማወጅ አለባቸው። አስ

ተጨማሪ አሳይ
Back to top button