ዜናማህበራዊ ጉዳይ

ዜና፡ “በሚሊዮን የሚቆጠር የትግራይ ህዝብ በሞት አፋፍ ላይ ነው፤ መንግስትም ሆነ የአለም አቀፉ ማህበረሰብ ድጋፍ ሊያደርጉ ይገባል” _ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር 

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 20/ 2016 ዓ/ም፡_ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር በክልሉ የተከሰተው አስካፊ ድርቅ ያሰከተለውን ተጽዕኖ በተመለከተ ትላንት አመሻሸ ባወጣው መገልጫ “በሚሊዮን የሚቆጠር የትግራይ ህዝብ በሞት አፋፍ ላይ ነው” ሲል አሰታውቋል።በትግራይ ከፍተኛ የረሃብ አደጋ እና ሞት ማንዣበቡን ያስታወቀው የክልሉ ግዚያዊ አስተዳደር ከ91 በመቶ በላይ የክልሉ ህዝብ ለከፋ ረሃብ እና ሞት ተጋልጧል በሏል። የትግራይ ጦረነት እና በከልሉ የተከሰተው ድርቅ ህዝቡን ለከፍተኛ አደጋ መዳረጉን ያመላከተው መግለጫው የሰብዓዊ እርዳታ መቋረጥም የነበረውን ከፍተኛ ቀውስ እንዲባባስ ማስቻሉን ጠቁሞ እርዳታው ቢጀምር እንኳ ያለው ፍላጎት እና አቅርቦት አንደማይጣጣም ገልጿል። በ1977 ዓ/ም በሚሊዮኖቸ የሚቆጥሩ ሰዎችን ለሞት ከዳረገው የድርቅ አዳጋ በኋላ አሁን በትግራይ ክልል የተከሰተው ድርቅ እጅግ አስከፊው መሆኑንም ነው መግለጫው የጠቆመው። ከፕሪቶያው የሰላም ስምምነተ በኋላ በሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ህዝብ በከፍተኛ የምግብ እጥረት መጠቃቱን የገለጸው መግለጫው ይህ አስካፊ የረሃብ አደጋ የሚገባውን ያህል ትኩረት አልማግኘቱን አመላክቷል። በዚህም ምክንያት ህጻናት፣ አረጋዊያን፣ ንፍሰ ጡር እና የሚያጠቡ እናቶች ለከፈተኛ ረሃብ እና ሞት ተዳርገዋል ሲል ጊዚያዊ አስተዳደሩ ገልጿል። በመገለጫው በሚሊዮን የሚቆጠር የክልሉ ህዝብ በሞት አፋፍ ላይ መሆኑ በመግለጽ በፌዴራልም ሆነ በክልል ደረጃ በክልሉ ህዝብ ላይ የተደቀነውን የረሃብ አደጋ ለመታደግ የሚያስችል እንቀሰቃሴ አለመኖሩን አመላክቷል። የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር አስቸኳይ የረሃብ አደጋ ጊዜ አዋጅ በማውጅ፤ ለአስቸኳይ ህይወት አድን የሚውል 50 ሚሊዮን ብር በመመደብ ችግሩን ለማቃለል ሲሰራ መቆየቱን በመጥቀስ ባለው አቅም ማነስ ችግሩን መቆጣጠር አልመቻሉን አሥታውቋል። በመሆኑም የፌዴራል መንግስቱም ሆነ የአለም ማህበረሰብ ህጋዊና ሞራላዊ ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ እና ህዝቡን እንዲታደጉ ጥሪ አቅረቧል።“ረሃብ ድምጽ አልባ ገዳይ ነው” ያለው መግለጫው አደጋው ጊዜ የማይሰጥ እና ህዝቡብ በየቀኑ በረሃብ እየሞተ በመሆኑ የፌዴራል መንግስትም ሆነ የአለም ማህበረሰብ ተገቢውን እርምጃ በተገቢው ጊዜ እንዲወሰዱ እና ህዝቡን ከሞት እንዲታደጉት ጥሪውን አስተላልፏል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button