ዜናጤናማህበራዊ ጉዳይ

ዜና፡ በአማራ ክልል የተከሰተው የጸጥታ ችግር የጤና ስራዎችን አስቸጋሪ ማደረጉንና ተላላፊና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች መስፋፋታቸውን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 20/ 2016 ዓ/ም፦ በአማራ ክልል የተከሰተው የጸጥታ ችግር የጤና ስራዎችን አስቸጋሪ ማደረጉን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ። 

የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አብዱልከሪም መንግሥቱ በሰላም እጦት ምክንያት ተላላፊና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች በማህበረሰቡ ላይ መስፋፋቱን ገልጿል፡፡

በሰላም በደፍረስ ሳቢያ አጥቢ እና ነፍሰ ጡር እናቶች ላይ ችግር እያጋጠመ መሆኑን የጠቀሱት ሃላፊው አልሚ ምግብ እና መድኃኒቶችን ለማቅረብ ለጤና ሚኒስቴር ጥያቄ ማቅረባቸዉን አስታውቀዋል። 

የጸረ ኤች አይ ቪ መድኃኒት ወደ ተለያዩ አካባቢዎች ለማድረስ መንገድ በመዘጋት ችግር ምከንያት 7 መቶ በላይ የመድኃኒቱ ተጠቃሚ የነበሩ የማህበረሰብ ክፍሎች መድሃኒቱን ማቋረጣቸውን አክለው ገልጸዋል። የሕጻናት ጤና አገልግሎት ክትባት ከ60 በመቶ ያልበለጠ መሆኑም ተመላክቷል። 

የወባ መከላከያ የቤት ውስጥ ኬሚካል ርጭት ከሚያስፈልጋቸው 30 ወረዳዎች በ6 ወረዳዎች ብቻ የተከናወነ መሆኑ እና አጎበር በማሰራጨት በኩልም አቅርቦት ስላልተገኘ እስካሁን አለመሰራጨቱን ቤሮው ጠቁመዋል።

የወባ በሽታ ለመከላከልና ለመቆጣጠር ጊዜያዊና ቋሚ ለወባ ትንኝ የመራቢያ ምቹ ቦታዎች ቢኖሩም ከፀጥታ ችግሩ ጋር ተያይዞ ተዘዋዉሮ ለመስራት አለመቻሉን አብዱልከሪም ተናግረዋል፡፡ የወባ በሽታ ቁጥር ካለፈዉ አመት ጋር ሲነፃፀር በዘንድሮዉ ዓመት ከፍተኛ ቁጥር ጭማሪ አሳይቷል፡፡

በክልሉ በተፈጠረው ግጭት ምክንያት 270 የጤና ተቋማት መዘረፋቸውን፤ ታካሚ እና መድኃኒት ማመላለሻ የነበሩ 43 አንቡላንሰ እና 17 ሌሎች መኪናዎች መዘረፋቸዉን ያስታወቀው የክልሉ ጤና ቢሮ ይህም ለጤና አገልግሎት አሰጣጥ ችግር ፈጥሯል ነው ያለው።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

በክልሉ ውስጥ የጤና ሥራዎችን ተደራሽ ለማድረግ የ341 ፕሮጀክቶች ግንባታ ቢኖርም 89 ብቻ ግንባታ ላይ መሆናቸዉ ነው የተገለጸው። 252 የጤና ተቋማት ፕሮጀክቶች በፀጥታ ችግር ምክንያት ሥራ ላይ አለመሆናቸውን ቢሮው አስታወቋል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button