ዕለታዊፍሬዜናፖለቲካ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና፡ ማይክ ሀመር በኢትዮጵያ ጉዳይ ለመምከር ወደ አውሮፓ ማቅናታቸው ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 15/2015 ዓ.ም፡- በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ መንግስት ልዩ ልዑክ የሆኑት ማይክ ሀመር ወደ አውሮፓ በማቅናት ከህብረቱ ሀገራት ጋር በኢትዮጵያ ወቅትዊ ሁኔታዎች እና በህዳሴ ግድብ ዙሪያ እንደሚመክሩ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በድረገጹ ባሰፈረው መረጃ አስታውቋል።

ማይክ ሀመር ለአንድ ሳምንት ያህል በስቶኮልም ስዊዲን እና ቤልጂየም ብራስልስ በሚኖራቸው ቆይታ በአውሮፓ ህብረት የኢትዮጵያ እና ሱዳን ተዎካዮች ጋር ተገናኘተው እንደሚመክሩ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ መረጃ አመላክቷል።

ማይክ ሀመር በመጀመሪያ በሲውዲን ስቶኮልም በተሰናዳው የአለም የውሃ ጉዳይ በሚክረው ውይይት ላይ እንደሚሳተፉ የጠቆመው መግለጫው በዚያውም በህዳሴ ግድብ ዙሪያ እንደሚመክሩ ገልጿል።

በመቀጠል ልዩ ልዑኩ ወደ ቤልጂየም ብራስልስ በማቅናት ከአውሮፓ ህብረት የኢትዮጵያ ተዎካዮች ጋር ተገናኝተው ህብረቱ እና አሜሪካ በኢትዮጵያ በአማራ እና በኦሮምያ ክልል የተፈጠረውን ቀውስ በሰላማዊ መንገድ መፍታት በሚያስችሉ መንገዶች ዙሪያ እንደሚወያዩ ጠቁሟል።   

ማይክ ሀመር በተጨማሪም ከህብረቱ ባለስልጣናት ጋር በትግራይ ሀይሎች እና በፌደራል መንግስቱ መካከል የተፈረመውን የሰላም ስምምነት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ በሚደረግበት ሁኔታ እና መደገፍ በሚቻልበት መንገድ ዙሪያ እንደሚወያዩም የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ መግለጫ አስታውቋል።

የአሜሪካ መንግስት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ ማይክ ሀመር በአውሮፓ የሚያካሂዱት ጉብኝት ከነሃሴ 13 ቀን 2015 ዓ.ም እስከ ነሃሴ 19 ቀን 2015 ዓ.ም እንደሆነም ተጠቁሟል። አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button