ዜናማህበራዊ ጉዳይ

ዜና፡ በሰሜን ሸዋ ዞን ሂዳቡ አቦቴ ወረዳ በመንግስት ጸጥታ ኃይሎች እና ኦነሠ ታጣቂዎች መካከል በተፈጸም ግጭት 14 ሰዎች ተገደሉ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 14/ 2016 ዓ/ም፡- በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሂዳቡ አቦቴ ወረዳ በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች እና በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂዎች መካከል በተካሄደ ግጭት 14 ሲቪል ሰዎች መገደላቸውን እና ከ10 በላይ መቁሰላቸውን ነዋሪዎች ለአዲስ ስታንዳርድ ተናገሩ። 

ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ላይ በሁለቱ ወገኖች መካከል በከባድ መሳሪያ በመታገዝ የተካሄደው ግጭት በኤጀሬ ከተማ እንዲሁም ቆቤ ጎዴ እና ላሉ ቀበሌ ለሶስት ቀናት መዝለቁን ነዋሪዎች ገልጸዋል። 

ስሙ እንዲጠቀስ ያለፈለገ ሰሜን ሸዋ ዞን ሂዳቡ አቦቴ ወረዳ የኤጄሬ ከተማ ነዋሪ ለአዲስ ስታንዳርድ እንደገለጸው “በከተማዋ ውስጥ ባሳለፍነው እሁድ ከጠዋት ጀምሮ እስከ 7፡00 በተካሄደው ከፍተኛ ውጊያ ሰባት ሰዎች ሲሞቱ ሌሎች ሰዎች ላይም ጉዳት ደርሷል”። 

በግጭቱ ከተገደሉ ሰዎች መካከል ከ12ኛ ክፍል ተማሪ እስከ የ70 አመት አዛውንት እንደሚገኙ ገልጾ የአምስት ለጆች አባት የሆነ ግለሰብም መገደሉን ነዋሪው ለአዲስ ስታንዳርድ ገልጿል። 

“በአካባቢያችን ያለው የሰላም ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ ነው። ህዝቡ ወጥቶ መግቢያ መንገድ አጥቷል።  በከተማዋ ውስጥ የጤና ጣቢያ፣ ትምህርት ቤቶች፣ የጉዞ አገልግሎቶች የሉም። ተፋላሚ ኃይሎቹ አሁንም ለውጊያ እራሳቸውን እያዘጋጁ መሆኑን እያየን ነው” በሏል። 

የላሉ ቀበሌ ነዋሪ በበኩሉ በቀበሌው በተካሄደ ተመሳሳይ ግጭት ስምንስ ሰዎች መሞታቸውን ለአዲስ ስታንዳርድ ገልጿል።

“በከባድ መሳሪያ ጭምር በታገዘው ተኩስ ልውውጥ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች የወረዳው ዋና ከተማ ወደሆነችው ፊቼ ተወስደው በፌቼ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ነው” ሲለ አክሎ ገልጿል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

 አዲስ ስታንዳርድ በዚህ ጉዳይ ላይ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የወረዳውን ኃላፊ ለማግኘት ያደረገው ጥረት አልተሳካም። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button