ዜናፖለቲካ

ዜና፡ ፖሊስ ከፖለቲከኛው በቴ ኡርጌሳ ግድያ ጋር በተያያዘ 13 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 4/ 2016 ዓ/ም፦ የምስራቅ ሸዋ ፖሊስ መምሪያ በኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር በቴ ኡርጌሳ ግድያ ጋር በተያያዘ 13 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ።

የምስራቅ ሸዋ ፖሊስ መምሪያ ረዳት ኮሚሽነር ታሪኩ ዲሪባ ከኦቢኤን ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ ግድያውን ለመመርመር የምርመራ ቡድን መቋቋሙን ተናግረዋል። 

በአንዳንድ መረጃዎች መሰረት በቁጥጥር ስር ከዋሉት 13 ተጠርጣሪዎች መካከል አንድ የበቴ ወንድም እና እህት ይገኛሉ።

ረዳት ኮሚሽነር ታሪኩ ዲሪባ የወንጀል ምርመራ ውጤት ይፋ እስደረግ ድርስ ህዝቡ በትዕግስት እንዲጠብቅ ጥሪ አቅርበዋል።

አቶ በቴ ማክሰኞ ለሊት ካረፉተብ ሆቴል ተወስደው በርካታ ጥይት ተተኩሶባቸው የተገደሉ ሲሆን በማግስቱ ጠዋት ላይ አስክሬናቸውን በመቂ ከተማ መንገድ ላይ ተጥሎ መገኘቱ ተገልጿል።

የቤተሰባቸው አባል፤ “የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች በሚመስሉ” ሰዎች ማክሰኞ ለሊት ካረፉበት ሆቴል መወሰዳቸው እና በማግስቱ አስክሬናቸው መንገድ ዳር ተጥሎ መገኘቱን ለአዲስ ስታንዳርድ ገልጸዋል። 

የኦሮሚያ ክልል መንግስት ረቡ ባወጣው መግለጫ፤ ለግድያው መንግሥትን ተጠያቂ ለማድረግ እየተካሄደ ያለው ፕሮፖጋንዳ ተቀባይነት የለውም ብሏል። 

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

የክልሉ መንግሥት በመቂ ከተማ እስከሬናቸው ተጥሎ የገኙት ፖለቲከኛ የተገደሉት “ባልታወቁ ጥቃት አድራሾች” እንደሆነም ገልጿል።

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን በበኩሉ በፖለቲከኛው ግድያ ዙሪያ ነጻ እና ገለልተኛ ምርመራ እንዲደረግ ጥሪ አቅርቧል። 

ኮሚሽኑ ግድያውን የፈጸሙ ግለሰቦች ተጠያቂ ለማድረግ የሚያስችል ምርመራ የፌደራል መንግስቱ እና የኦሮምያ ክልላዊ መንግስት ማከናወን ይገባቸዋል ሲል አሳስቧል።

ፓርቲያቸው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ከግድያው ጋር በተገናኘ ባወጣው መግለጫ ድርጊቱን በጽኑ አውግዞ ገለልተኛ እና ነጻ ምርመራ እንዲከናወን ጠይቋል።

በተጨማሪም የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና  የአሜሪካ ሴኔት ውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ የበቴ ኡርጌሳ ግድያ በገለልተኛ ወገን እንዲጣራ ጠይቀዋል። 

የአራት ልጆች አባት የሆኑት በቴ ስስርዓተ ቀብራቸው ትላንግ ሚያዚያ 3 ቀን  ከቀኑ 6፡00 ላይ በትውልድ ከተማቸው መቂ መሰረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ተፈጽሟል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button