ዜናማህበራዊ ጉዳይ

ዜና፡ ህጻናት ተማሪዎች ከጦርነት ስነልቦና እንዲያገግሙ ለማስቻል ያለመ የስዕል ኤግዚቢሽን በዩኤስ ኤድ አስተባበሪነት ቀረበ

አዲስ አበባ፣ ጥር 16/2016 ዓ.ም፡- ስዕል ከጦርነት ሥነልቦና ማገገሚያ ሁነኛ መንገድ ነው በሚል በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በተካሄደባቸው ሶስት ክልሎች በሚማሩ ተማሪዎች ተስለው የተመረጡ 56 ስዕሎችን በአዲስ አበባ ሒልተን ሆቴል በዩኤስ ኤድ አስተባበሪነት የስዕል አውደ ርዕይ ቀርበዋል።

ብሩህ መጻኢ በሚል ርዕስ በሒልተን ሆቴል ለእይታ የቀረበው የስእል አውደ ርዕይ የጦርነት ጠባሳን ለማከም ስዕል ያለውን ሚና የሚያጎላ ነው ተብሏል።

ፕሮግራሙ የተጀመረው ከሁለት አመታት በፊት መሆኑን እና አላማውም በአማራ፣ ትግራይ እና አፋር ክልሎች በጦርነቱ ሳቢያ ተፈናቅለው በመጠለያ ካምፖች የነበሩ ተማሪዎችን በስዕል የመንፈስ ጥንካሬ እንዲላበሱ እና ከጦርነቱ እንዲያገግሙ ለማስቻል መሆኑም ተጠቁሟል።

በክልሎቹ በሚገኙ 156 የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቱ የሚማሩ ተማሪዎችን ያሳተፈ የስእል ውድድር መዘጋጀቱን የጠቆመው መግለጫው ተማሪዎች ከጦርነቱ ጋር በተያያዘ ያሳለፉትን ሁኔታ እንዲያንጸባርቁ እድል መፈጠሩን ጠቁሟል።

በስዕል አውደ ርዕዩ በ4ኛ እና በ5ኛ ክፍል ተማሪዎች የተሳሉ የገጠር መንደሮች፣ አትሌቶች፣ ትምህርት ቤቶች እና ሌሌሎች ስዕሎች ለእይታ ቀርበዋል።

የስዕል ኤግዚቢሽኑ ከጥር 14 ቀን 2016 ዓ.ም እስከ ጥር 20 ቀን 2016 ዓ.ም ለታዳሚዎች ክፍት ሆኑ እንደሚቆይ ተመላክቷል።

በአውደ ርዕዩ መክፈቻ የትምህርት ሚኒስቴር እና የሴቶችና ሕጻናት ሚኒስትር ዴኤታዎች፣ የአሜሪካ ኤምባሲ ምክትል አምባሳደር እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል። አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button