ዜና

ዜና፡ የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ሁለት ስምምነቶችን ተፈራረመ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 21/ 2016 ዓ/ም፦ የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን በዛሬው ዕለት የካፒታል ገበያ መሠረተ ልማቶችን ለማጠናከር፣ ግልጽነትን ለማጎልበት እንዲሁም የቴከኖሎጂ አቅምን ለማዳበር የሚረዱ ሁለት ስምምነቶችን ከተላያዩ የፌዴራል ተቋማት ጋር መፈራረሙን አስታወቀ።

የመጀመሪያው ስምምነት “የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ተአማኒነት ግብረ ኃይል” ስምምነት ሲሆን ስምምነቱም በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትህ ሚኒስቴር ፣ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ፣ የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ፣ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን፣ እንዲሁም የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት መካከል የተደረገ መሆኑን ባለስልጣኑ ገልጿል።

የስምምነቱ ዓላማ የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያን ህጋዊ እና ከወንጀል ድርጊቶች የጸዳ ለማድረግ በተቋማቱ መካከል ቋሚና ቀልጣፋ ቅንጅታዊ የአሰራር ስርዓት ለመዘርጋት እንዲሁም ውጤታማ የሕግ ማስከበር ስርዐት በመፍጠር የካፒታል ገበያውን ተዐማኒነት ማረጋገጥ ነው።

በስምምነቱ መሰረትም ግብረ ኃይሉ ማጭበርበር ባለበት ሁኔታ እና በሕገወጥ የአክሲዮን አቅርቦት ላይ የተሰማሩ፣ እና በርካታ ኢንቨስተሮች ገንዘባቸውን እንዲያጡ ምክንያት የሆኑ አከስዮን ሻጮችን በመለየት ለፍርድ የማቅረብ ኃላፊነት ያለበት መሆኑ ተመላክቷል።

ሁለተኛው ስምምነት የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣንን በቴከኖሎጂ ለመደገፍ የተደረገ የትብብር መግባቢያ ስምምነት መሆኑን የገለጸው ባለስልጣኑ ስምምነቱ በየኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ፣ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አጄንሲ ፣ የአርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ ኢንስቲትዩት እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ መታወቂያ አገልግሎት መካከል የተደረገ ነው ብሏል። 

ከሳይበር ደህንነት ጋር የተያያዙ የቴክኖሎጂ ድጋፎችን ያካተተው ስምምነቱ የባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱን የገበያ መቆጣጠር እና የኢንቨስተሮችን ደህንነት የመጠበቅ አቅሙን ለማሳደግ ያለመ ነው ተብሏል። 

ዘመናዊ ቴከኖሎጂን በመጠቀም ሊከሰቱ የሚችሉ አደጋዎችን በንቃት ለመከታተል እና ለመቅረፍ እንዲሁም አጠቃላይ የቁጥጥር ማዕቀፉን ለማሳደግ ባለሥልጣኑ ዓላማ እንዳለው አክሎ ገልጿል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

እነዚህ ስምምነቶች የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን በአዋጅ ቁጥር 1248/2013 ከተሰጡት ሥልጣን እና ተግባራት መካከል አንደኛው አና ዋነኛ የሆነውን የካፒታል ገበያው ተኣማኒ እንዲሆን ማድረግ እና መዋቅራዊ የአደጋ ስጋቶችን የመቀነስ አላማ በቀጥታ ከመደገፍም ባለፈ ለኢንቨስተሮች ተገቢውን ጥበቃ ወይም ከለላ ለመስጠት ይረዳሉ ሲል አስታውቋል።አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button