አዲስ አበባ፣ መጋቢት 23/2016 ዓ.ም፡- በብሪታንያ የሚገኝ ሙዚየም ከኢትዮጵያ የተዘረፉ እና ለእይታ አቅርቧቸው በማያውቀው 11 ታቦቶች ዙሪያ ምርመራ ሊካሄድበት መሆኑ ተጠቆመ።
በመቅደላው ጦርነት ወቅት በእንግሊዝ ወታደሮች ተዘርፈው የተወሰዱት 11 የዲንጋይ እና የእንጨት ታቦቶች በሙዚየሙ ለእይታ ቀርበው እንደማያውቁ መገለጹን የጠቆመው የጋርድያን ዘገባ የሙዚየሙ ባለስልጣናትም ሆኑ ጠባቂዎቹ የተቀደሰ ሃይማኖታዊ ቅርስ ነው በሚል መርምረውት እንደማያውቁ አመላክቷል።
በሙዚየሙ የሚገኙት ታቦቶች ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ በተደጋጋሚ ጥያቄ ይቀርብ እንደነበር የጠቆመው ዘገባው ከአምስት አመታት በፊት የኢትዮጵያ የባህል ሚኒስቴር እንግሊዝን በጎበኙበት ወቅት ያቀረቡትን ጥያቄ በአብነት ጠቅሷል።
ከታቦታቱ ጋር በተያያዘ ለሙዚየሙ ጥያቄ ቢቀርብለትም የሰጠው ምላሽ ግን የተድበሰበሰ ነው በሚል ለሀገሪቱ የኢንፎርሜሽን ተቆጣጣሪ ቢሮ (Information Commissioner’s Office) የጉዳዩ ተሟጋቾች ቅሬታ ማቅረባቸውን ዘገባው አመላክቷል።
ቅርስ አስመላሽ የተባለ መንግስታዊ ያልሆነ ድጅት መረጃ የማግኘት መብቱን ተጠቅሞ ባሳለፍነው አመት 2015 ዓ.ም ነሃሴ ወር ላይ ጥያቄ ማቅረቡን ያስታወቀው ጋርድያን ጋዜጣ ሙዚየሙ የሰጠው ምላሽ ግን የተድበሰበሰ እና ዋነኛ ጉዳዮችን ያልዳሰሰ ነበር ሲል መግለጹን አካቷል።
በሙዚየሙ የሚገኙት ታቦታቱ ለእይታም ሆን ለጥናት የሚቀርቡ ባለመሆናቸው በዝግ ክፍል ውስጥ ተቀምጠው በኢትዮጵያውያን ካህናት ብቻ እንዲጎበኙ የሚደረጉ በመሆኑ ወደ መጡበት ሊመለሱ ይገባል የሚል እምነት እንዳለው የቅርስ ተቆርሪ ተቋሙ ማኔጂንግ ዳይሬክት ልዊስ ማክናውት መናገራቸው ዘገባው አስታውቋል።
በጉዳዩ ዙሪያ አስተያየት እንዲሰጥ የተጠየቀው ሙዚየሙ ምላሽ ለመስጠት ፍቃደኛ አለመሆኑን የጠቆመው ዘገባው ሙዚየሙ ያቀረበው እቅድ መብሪታንያ ለሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ አብያተክርስቲያናት ለረዝም ግዜ የሚቆይ በውሰት መስጠት መሆኑን አመላክቷል። አስ