ዜናፖለቲካ

ዜና: “የፕሪቶርያው ስምምነት ትግበራ በየደረጃው ድርድር የሚያስፈልገው ነው እንጂ ልሙጥ የሆነ አይደለም” - ጀነራል ታደሰ ወረደ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 9/2016 ዓ.ም፡- የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዝዳንት ጀነራል ታደሰ ወረደ ትላንት ሚያዚያ 8 ቀን 2016 ዓ.ም በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የፕሪቶርያው ስምምነት ሁሉንም ችግሮች የሚፈታ አይደለም ሲሉ ገልጸዋል። የፕሪቶርያው ስምምነት ትግበራ በየደረጃው ድርድር የሚያስፈልገው ነው እንጂ ልሙጥ የሆነ አይደለም ሲሉ በአተገባበሩ ዙሪያ ስለሚታዩ ችግሮች አብራርተዋል። የፕሪቶርያውን ስምምነት እንደመታገያ አድርገን ለመጠቀም የተቀበልነው ስምምነት ነው ብለዋል።

በሌላ መልኩ የፕሪቶርያው ስምምነት በአሸናፊ እና ተሸናፊ መካከል የተደረገ አልነበረም ያሉት ጀነራሉ በሁለት ተፋላሚ ሀይሎች መካከል የተደረገ ነው፤ በስምምነቱ ላይ ሁሉም የምንፈልጋቸው ነጥቦች አይደሉም የተካተቱት፤ በፌደራል መንግስቱም በኩል እንዲሁ ብለዋል።

አሁን በመታየት ያለው ውጤት የጦርነቱ ውጤት እንጂ የጦርነቱ መነሻ አይደለም ሲሉ ገልጸዋል።

ከስምምነቱ አበይት ነጥቦች መካከል በሀይል ተይዘው በሚገኙ የትግራይ ግዛታዊ አንድነት ጉዳዮች ናቸው ሲሉ ያብራሩት ጀነራል ታደሰ በስምምነቱ የተፈራረምነው በህገመንግስቱ መሰረት ይፈታል የሚል ነው፤ እስካሁን ተነክቶ የማያውቀው የስምምነት ክፍል እሱ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

የአማራ ክልል መንግስት ቦታዎቹን በሀይል ይዞ የመቆየት ፍላጎት አለው ያሉት ጀነራሉ ነገር ግን የተፈራረምነው ከፌደራል መንግስቱ ጋር በመሆኑ ግንኙነታችን ከሱ ጋር ነው። ከጦርነቱ በፊት የትግራይ ግዛት የነበሩ አከባቢዎች ይመለሱ የሚለው አቋማችን የጸና ነው፤ በዚህ ጉዳይ ምንም አይነት ምክንያተ እንደማንቀበል ግልጽ ነው ሲሉ አስታውቀዋል።

የፌደራል መንግስት አከባቢዎቹ በፌዴራል ስር ቆይተው ሪፈረንደም ይካሄድ’ የሚል አቋም ያለው ሲሆን በእኛ በኩል ደግሞ በአከባቢው ጊዚያዊ አስተዳደር ተቋቁሞ ወደ ትግራይ ይመለሱ የሚል አቋም ነው ያለን ብለዋል።

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዝዳንት ጀነራል ታደሰ ወረደ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በምዕራብ ትግራይ፣ ጸለምት እና በአንዳንድ የደቡብ ትግራይ አከባቢዎች ያሉት በአማራ ክልል የተመሰረቱት አስተዳደሮች እንዲፈርሱ ከፌደራል መንግስት ጋር ስምምነት ተደርሷል ብለዋል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

የሂደቱ የመጀመሪያው ምዕራፍ ኢህገመንግስታዊ በሆነ መንገድ የተመሰረቱት አስተዳደሮች እንዲፈርሱ ማድረግ እና ታጣቂዎችን ትጥቅ ማስፈታት ነው ያሉት ጀነራሉ ከዚያም የፍትህ ስርአቱን መመለስ ይሆናል ሲሉ ገልጸዋል።

ደቡብ ትግራይ ጋር በተያያዘ ሁኔታው መለወጥ እንዳለበት ብናምንም በሀይል ልናደርገው አንፈልግም፣ ለምሳሌ ኮረም አከባቢ የተወሰኑ የፖሊስ ሀይሎች ብቻ እንዳሉ እናውቃለን፤ እዚያ አከባቢ ያለውን የመከላከያም ይሁን የፌደራል ፖሊስ በሀይል የማስለቀቅ ተልእኮ የተሰጠው ሀይል የለንም ሲሉ አብራርተዋል።

በርተክላይ፣ ጨርጨርም ይሁን ቺኮማጆ የተቀመጠ ሀይል አለን ነገር ሲሉ የጠቆሙት ጀነራል ታደሰ ነገር ግን በዘላቂነት መፍትሔ እንዲያገኝ ነው የምንፈልገው፤ ይህን ከግምት ውስጥ አስገብተን ነው የምንቀሳቀሰው፣ ከፌደራል መንግስቱ ጋር በተስማማንበት መልኩ ነው መሄድ የምንፈልገው ብለዋል።

ተፈናቃዮች ሲመለሱ ክብራቸው ተጠብቆ፣ የሚያስፈልጋቸው መሰረተ ልማት ሁሉ ተሟልቶ፣ ሰብአዊ ድጋፍ ጨምሮ የተለያዩ ድጋፎች በማድረግ መሆን አለበት  ያሉት ጀነራሉ  አስተዳደርን በሚመለከት ቀበሌዎችና ወረዳዎችን የሚያስተዳድሩ ጊዚያዊ  አስተዳደሮች ራሱ ህዝቡ እንደሚመርጥ አስታውቀዋል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button