ዜናፖለቲካማህበራዊ ጉዳይ

ዜና፡ የአለም የምግብ ፕሮግራም በአማራ ክልል በዘጠኝ ዞኖች ተንቀሳቅሶ ለመስራት መቸገሩን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10/2016 .ም፡ በፌደራል መንግስቱ እና በትግራይ ሀይሎች መካከል የተደረሰው የሰላም ስምምነት በአፋር እና በትግራይ ክልሎች አንጻራዊ ሰላም በመስፈኑ በተገቢው መንገድ መንቀሳቀስ መቻሉን ያስታወቀው የአለም የምግብ ፕሮግራም በአማራ ክልል በዘጠኝ ዞኖች ግን በአሁኑ ወቅት በትጥቅ የተደገፈ ከፍተኛ ግጭት በመኖሩ እንቅስቃሴው መገደቡን አመላክቷል። የአለም የምግብ ፕሮግራም በክልሉ የሚገኙ ሰራተኞቹን ደህንነት ለማስጠበቅ እና ንብረቶቹ እንዳይዘረፉ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን አስታውቋል።

ድርጅቱ ትላንት ጥቅምት 9 ቀን 2016 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ በኢትዮጵያ ለማቀርበው የምግብ እርዳታ የገንዘብ እጥረት ከፍተኛ ችግር ፈጥሮብኛል ሲል ጠቁሞ እስከ አመቱ አጋማሽ ድረስ የረድኤት አቅርቦቱን በአግባቡ ለማከናወን ከሚያስፈልገው ገንዘብ ውስጥ 219 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር እጥረት እንደገጠመው አስታውቋል።

በዚህም ሳቢያ በኢትዮጵያ የምግብ እርዳታ ከሚያስፈልጋቸው ውስጥ 50 በመቶ ለሚሆኑት ብቻ ለማቅረብ መገደዱን ጠቁሟል።

እስከ ጥቅምት መጨረሻ ድረስ በኢትዮጵያ አስቸኳይ የምግብ እርዳታን የሚጠባበቁ ሰዎች ቁጥር ከ15 ሚሊየን እንደሚበልጥ አስታውቋል። ከነዚ ውስጥም 11 ሚሊየን የሚሆኑት የምግብ ችግር ያለባቸው፣ ከቀያቸው የተፈናቀሉ፣ ወደ ቀያቸው የተመለሱ እንደሚገኙበት እና የመንግስታቱ ድርጅት የረድኤት ተቋምን ጨምሮ ሌሎች በጎ አድራጎት ድርጅቶች ቅድሚያ ተሰጥቷቸው አቅርቦቱ የሚሟላላቸው መሆናቸውን አመላክቷል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button