ዜናፖለቲካ

ዜና፡ የሲዳማ ክልል መንግስት ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ያዋልኩት ህጋዊ አሰራርን በመከተል ነው ሲል ገለፀ፤ ሲ.ፌ.ፓ ተጨማሪ አራት አባላት መታሰራቸውን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 24/ 2016 ዓ.ም፡- የሲዳማ ፌዴራሊስት ፓርቲ አባላት በቁጥጥር ስር የዋሉት ህጋዊ አሰራርን በተከተለ መንገድ መሆኑን የሲዳማ ክልል ሰላም እና ደህንነት ኃላፊ አቶ አለማየሁ ጦሞቲዮስ ለአዲስ ስታንዳርድ ገለፁ፡፡

የክልሉ ሰላም እና ደህንነት ኃላፊ አቶ አለማየሁ ጦሞቲዮስ ለአዲስ ስታንዳርድ በስልክ በሰጡት መረጃ “ሲዳማ ፌዴራሊስት ፓርቲ በክልሉ መንግስት አባላቶቼ ያለ ፍርድ ቤት መዘዣ የህግ አሰራርን ባልተከተለ መንገድ በቁጥጥር ስር ውለውብኛል” ሲል የሰጠውን ቃል “ሀሰት ነው” ሲሉ አጣጥለዋል፡፡

ፓርቲው ሶስት አባላቱ ያለ ፍርድ ቤት ማዘዣ ነው የታሰሩት ሲል ለአዲስ ስታንዳርድ መግለፁ የሚታወስ ሲሆን የክልሉ የሰላምና ደህንነት ኃላፊ ማንኛውንም ተጥርጣሪ ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ አናስርም ሲሉ ገልፀው እስሩም ሆነ የቤት ፍተሸ ያደረግነው የፍርድ ቤት ትዕዛዝን ተከትለን ነው በለዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እያለ የሲዳማ ፌዴራሊስት ፓርቲ ጽ/ ቤት ኃላፊ አቶ ገነነ ሃሳና ቀደም ሲል ከታሰሩበት ሶስት አባላት በተጨማሪ ሌላ አራት አባላቱ በክልሉ መንግስት መታሰራቸውን ለአዲስ ስታንዳርድ ገልፀዋል፡፡ አቶ ገነነ እንደገለፁት ኤሊያስ ፌዶ የተባሉት አባል በሀገረ ሰላም እንዲሁም ሃጎሲ ወጎ በባንሳ ወረዳ በስራ ላይ ሳሉ በትላንትናው እለት ታስረዋል፡፡ በተጨማሪም አሲደሰች ማርማራ እና ተስፋዬ ታገል በጊርጃ ሆኮ ወረዳ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ኃላፊው ለአዲስ ስታንዳድር ገልፀዋል፡፡

የክልሉ ሰላም እና ደህንነት ኃላፊ ከአዲስ ስታንዳረድ ጋር ባደረጉት የስልክ ቆይታ “ አሁንም ቢሆን በሚዲያ እየመጡ የሚያተራምሱትን የገቡበት ገብተን በወንጀላቸው ልክ እንዲጠየቁ እናደርጋለን” ሲሉ ተናግረዋል፡፡ የፓርቲ አባልና አመራር መሆን ከተጠያቂነት አያስመልጥም ያሉት አቶ አለማየው እንኳን የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት ይቅርና ለህዝብ ደህንነትና አብሮነት የማይሰሩ የብልፅግና አባላትንም እያሰርን ነው ብለዋል፡፡

ፓርቲው ሰሞኑን ባወጣው መግለጫ የክልሉ መንግስት በፀጥታና ደህንነት ቢሮዎች አማካይነት በጫንጌ ካምፕ የነበረውን የክልሉን ልዩ ሀይል አባላትን በመጠቀም ህዝቡ ላይ ጉዳት ለማድረስ አቅዷል ሲል ከሷል፡፡ ይህን በተመለከተ አቶ አለማየሁ “መንግስት የራሱን ሀይል ህጉ በሚፈቅደው መንገድ ለፈለገው አላማ እንደ ፈለገው ማደራጀት ይችላል” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ አክለውም የተደራጀው ሀይል እነሱ ላይ ያደረሰው ጥቃት ካለ ማስረጃ ይዘው በጠየቅ ይችላሉ፤ ካዛ ውጭ በአሉባልታ የሚያነሱት ነገር የክልሉን መንግስት ገፅታ ለማጠልቸት እንጂ መሬት ላይ ያለ ነገር አይደለም ብለዋል፡፡

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

አቶ አለማየሁ የተደራጃ ሀይል አለ ስለሚባለው ነገር የሚያውቁጥ ነገር አለመኖሩንም የገለፁ ሲሆን በሲዳማ ክልል ልዩ ሃይል የሚባል ሀይል አለመኖሩን እና ያለው መደበኛ የፖሊስ አደረጃጀት መሆኑን ለአዲስ ስታንዳርድ ገልፀዋል፡፡ ፓርቲው ይህን የሚያደርገው ያለማስረጃ መሆኑን እና የክልሉን ስም ለማጠልሸት የሚያደርጉት ጥረት ነው በማለት ገልፀዋል፡፡

“ሲዳማ ፌዴራሊስት ፓርቲ አባላት በፓርቲ ሽፋን የክልሉ ሰላምን የማደፍረስ አላማ ያነገቡ ናቸው” ሲሉ የከሰሱት ኃላፊው በግል ስሜት በመነሳሳት አገርን የሚያፈርሱ ድርጊቶችን ከሚከውኑ አካላት ጋር ህዝቡ እንዳይተባበር ጥሪ አቅርበዋል፡፡አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button