ዜናፖለቲካ

ዜና፡ በሱዳን የእርስ በርስ ጦርነት በሁለቱም ወገኖች የዘር ማጽዳት እና የጦር ወንጀል ተፈጽሟል ስትል አሜሪካ ገለጸች

አዲስ አበባ፣ ህዳር 27/2016 ዓ.ም፡- የሱዳን ተቀናቃኝ ሀይሎች በዳርፉር እያካሄዱት በሚገኘው የእርስ በርስ ጦርነት የዘር ማጽዳት እና የጦር ወንጀል ፈጽመዋል ስትል አሜሪካ ገለጸች። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያቤት ባካሄደው ምዘና ወንጀሉ ተፈጽሟል ሲሉ አንቶኒ ብሊንከን መናገራቸውን ኤኤፍፒ የዜና አውታር ዘግቧል።

የፈጥኖ ደራሽ ሀይሉ በዳርፉር በሚኖሩ በአፍሪካውያኑ የማሳሊት ጎሳዎች ላይ ከአረብ ሀይሎች እና በአከባቢው ከሚንቀሳቀሱ ሚሊሻዎች ጋር በመተባበር የጅምላ ጭፍጨፋ ፈጽሟል ሲል የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ መግለጹን ዘገባው አመላክቷል።

ከ20 አመታት በፊት በአከባቢው የተካሄደውን የዘር ማጥፋት ወንጀል የሚያስታውስ ተግባር ነው ሲሉ አንቶኒ ብሊንከን መናገራቸውን አስታውቋል።

የማሳሊት ጎሳ አባላት እየታደኑ መገደላቸውን እና አስከሬናቸው በየመንገዱ እንዲሰጣ መደረጉን፣ ቤቶቻቸው በእሳት መንደዳቸውን፣ በሱዳን ለእነሱ የሚሆን መኖሪያ የለም መባላቸውን ብሊንከን ተናግረዋል ያለው ዘገባ ወሲባዊ ጥቃትም እንደተፈጸመባቸው መግለጻቸውን አስታውቋል።

ሁለቱም ተቀናቃኝ ሀይሎች አስከፊ ግፎችን ፈጽመዋል፣ ግድያና ውድመትን በሱዳን ላይ አድርሰዋል ሲሉ ብሊንከን መግለጻቸውንም ዘገባው አካቷል። ሁለቱም ሀይሎች ጦርነቱን እንዲያቆሙ፣ ለአለም አቀፍ ህግ ተገዢ እንዲሆኑ እና ወንጀሉን የፈጸሙትን ተጠያቂ እንዲያደርጉ ማሳሰባቸውን አስታውቋል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button