ዜናፖለቲካ

ዜና፡ ከ85ሺ በላይ የሱዳን ስደተኞች የኢትዮጵያን ድንበር አቋርጠው መግባታቸው ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7/2016 ዓ.ም፡- በሱዳን ከተቀሰቀሰው ግጭት ጋር በተያያዘ ቀያቸውን ለቀው፣ የኢትዮጵያን ድንበር አቋርጠው የተሰደዱ ሰዎች ቁጥር ከ85ሺ በላይ መድረሱን አለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት አይኦኤም አስታወቀ።

እስከ እሁድ ጥቅምት 4 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ የኢትዮጵያን ድንበር አቋርጠው ከገቡ 85ሺ 400 ስደተኞች ውስጥ 38ሺ 560 የሚሆኑት ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን የጠቆመው አይኦኤም 31ሺ 115 የሚሆኑት ደግሞ ሱዳናውያን መሆናቸውን አመላክቷል። ቀሪዎቹ 15ሺ 821 የሚሆኑት ከሶስተኛ ሀገር ዜጎች ሲሆን በግጭቱ ሳቢያ ከሱዳን ተሰደው ኢትዮጵያ የገቡ መሆናቸውን ጠቁሟል።

ስደተኞቹ በዋናኛነት የሚያቋርጡት የኢትዮጵያ ድንበር መተማ እና ኩርሙክ መሆኑን ያመላከተው አለምአቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት አይኦኤም 35ሺ 440 የሚሆኑት ሴቶች መሆናቸውን አስታውቋል፤ ቀሪዎቹ 50ሺ 56 የሚሆኑት ደግሞ ወንዶች።

ስድስተኛ ወሩን ባስቆጠረው የሱዳን እርስ በርስ ግጭት ከቀያቸው የተፈናቀሉ ሱዳናውያን ቁጥር ከሰባት ሚሊየን መብለጡን አለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት መረጃ ያሳያል። ከነዚህ ውስጥ በግጭቱ ሳቢያ ብቻ አራት ነጥብ አምስ ሚሊየን ሱዳናውያን መፈናቀላቸውነ አመላክቷል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button