ዜናፖለቲካቢዝነስ

ዜና፡ ለአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ 188 ባለኮከብ ሆቴሎች አስፈላጊውን ዝግጅት አጠናቀዋል ተባለ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 4/2016 ዓ.ም፡- በ37ኛው ኅብረት የአፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ለመሳተፍ የሚመጡ እንግዶችን ተቀብሎ ለማስተናገድ ሆቴሎች አስፈላጊውን ዝግጅት አጠናቀናል ማለታቸው ተጠቆመ።

በጉባኤው ለመሳተፍ ወደ አዲስ አበባ የሚመጡ እንግዶችን ለመቀበል 188 ባለ ኮከብ ሆቴሎች አስፈላጊውን ዝግጅት አድርገዋል ሲሉ አቶ ጌታሁን አለሙ የኢትዮጵያ ቱሪዝምና ሆቴል ማርኬት ማኅበር ፕሬዚዳንት እንደነገሩት የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘግቧል።

ሆቴሎች የአገልግሎት ምቹ አካባቢን በመፍጠር እንግዶችን ተቀብሎ ለማስተናገድ ዝግጁ መሆናቸውን ጠቅሰው፣ እንግዶችን ያለምንም የጸጥታ፣ የውሃ፣ የስልክ፣ የመብራትና ሌሎች አገልግሎቶች ችግር ለማስተናገድ መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል ብሏል።

በሆቴሎች እንግዶችን ተቀብሎ ለማስተናገድ የተለያዩ ዝግጅቶች እንደሚደረጉ ጠቅሰው፣ ባለ ኮከብ ሆቴሎች ለእንግዶች ምቹ አገልግሎቶችን ለመስጠት የሚያስችል ዝግጅት ማድረጋቸውን አመላክተዋል።

ለጉባኤው ተሳታፊዎች ትክክለኛ የትራንስፖርት፣ የመረጃና፣ የሆቴል አገልግሎቶችን መስጠት ተገቢ መሆኑን የገለጹት ፕሬዚዳንቱ በተለይም ለተሳታፊዎች የመጓጓዣ አማራጮችን ማቅረብ እንደሚገባም ጠቁመዋል።

ማኅበሩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ወደ መዲናዋ ለሚመጡ እንግዶች የከተማዋን የቱሪስት መዳረሻዎች ለማስተዋወቅ እንደሚሠራ ጠቅሰው፣ እንግዶች በቆይታቸው የአንድነት፣ ወዳጅነትና፣ እንጦጦ ፓርኮችን ጨምሮ የተለያዩ መዳረሻዎችን እንዲጎበኙ ለማድረግ እንደሚሠራ ጠቁመዋል።

በአዲስ አበባ የካቲት 9 እና 10 ቀን 2016 ዓ.ም በሚካሄደው የአፍሪካ ህብረት 37ኛው የመሪዎች ስብሰባ ላይ የ34 የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች እና ከፍተኛ ባለስልጣናት እንደሚካፈሉ ማረጋገጫ መስጠታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ አለም ጥር 30 ቀን 2016 ዓ.ም በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ   መናገራቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

37ኛው የህብረቱ የመሪዎች ጉባኤ ላይ እንደሚካፈሉ ማረጋገጫ ከሰጡ ሀገራት ውስጥ 24 የአፍሪካ ሀገራት በፕሬዝደንቶቻቸው፣ 5 ሀገራት በምክትል ፕሬዝዳንቶቻቸው፣ ሁለት ሀገራት በጠ/ሚኒስትሮቻቸው እና ሁለት የአፍሪካ ሀገራት ደግሞ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቻቸው ተወክለው ይሳተፋሉ ማለታቸውም በዘገባው ተካቷል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button