ዜናፖለቲካ

ዜና፡ ሶማሊያ እና ቱርክ ወታደራዊ ስምምነት መፈራረማቸው ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 1/2016 ዓ.ም፡- በኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ የተደረሰውን የባህር በር ስምምነት ተከትሎ ግንኙነቷ የሻከረው ሶማሊያ ከቱርክ ጋር ወታደራዊ ስምምነት መፈራረሟ ተገለጸ።

የመከላከያ እና የኢኮኖሚ ትብብር ማዕቀፍ በሚል ሁለቱ ሀገራት የተፈራረሙት ስምምነትን በሶማሊያ በኩል የሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስትር አብዱልከዲር ሞሃመድ ኑር እንዲሁም ቱርክን በመወከል የሀገሪቱ የመከላከያ ሚኒስትር ያሳር ጉለር መፈረማቸው ታውቋል።  

የተፈራረምነው ስምምነት ሽብርተኝነትን በጋራ ለመዋጋት እና ወታደራዊ የፋይናንስ ትብብር ማድረግ የሚለውንም ያካተተ ነው ሲሉ የቱርኩ መከላከያ ሚኒስትር በስምምነት ፊርማው ወቅት ተናግረዋል።  

ምምነቱ ሶማሊያን የበለጠ ተጠቃሚ ያደርጋታል ብለን እናምናለን ሲሉ ገልጸዋል። የሁለቱ ሀገራት መከላከያ ሚኒስትሮች ተገናኝተው መወያየታቸው ብቻ ውጤታማ ነው ሲሉ የገለጹት የቱርኩ መከላከያ ሚኒስትር ስምምነቱ የሁለቱን ሀገራት ወታደራዊ ግንኙነት ይበልጥ ያጠናክረዋል ሲሉ ተናግረዋል።

ሶማሊያ በአፍሪካ ካሉን አጋሮች ወነኛዋ ናት ሲሉ የገለጹት ያሳር ጉለር ሀገራቸው የሶማሊያን ሉአላዊነት እና የግዛት አንድነት እንዲከበር እገዛዋን እንደምታደርግ የደረሰችው አቋም አንጸባርቀዋል።

የሶማሊያው መካለከያ ሚኒስትር አብዱልከዲር ሞሃመድ ኑር ትምህርታቸውነ የተከታተሉት በቱርክ መሆኑን አልሞኒተር በዘገባው አስታውቋል። አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button