ዜናፖለቲካ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና፡ የኢትዮጵያና ሶማሊያ መሪዎች በመካከላቸው የተፈጠረውን ውጥረት እንዲያረግቡ አሜሪካ ጠየቀች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 14/2016 ዓ.ም፡- የአሜሪካ መነግስት የአፍሪካ ጉዳዮች ምክትል ጸሐፊ ሞሊ ፊ ከአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሀመር ጋር በመሆን ትላንት የካቲት 13 ቀን 2016 ዓ.ም በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ኢትዮጵያና ሶማሊያ መሪዎች በመካከላቸው የተፈጠረውን ውጥረት እንዲያረግቡ አሳስበዋል።

ምክትል ሀላፊዋ በአዲስ አበባ እና ሞቃዲሾ በመገኘት ከሁለቱ ሀገራት መሪዎች ጋር መወያየታቸውን እና መሪዎቹ በተሻለ ሁኔታ እንዲነጋገሩ ለማገዝ መጣራቸውን አስታውቀዋል።

ቀጠናው ሌላ ጦርነት ሊያስተናግድ አይገባውም ያሉት ጸሃፊዋ ኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ የተፈራረሙትን የመግባቢያ ሰነድ ተከትሎ የተፈጠረው ውጥረት መርገብ ይገባዋል ሲሉ አሳስበዋል።

ኢትዮጵያ ለንግድ አገልግሎት የሚውል ወደብ ለማግኘት የምታደርገው ጥረት ተገቢነት ያለው ቢሆንም ከሶማሊያ ፌደራል መንግስት ጋር በመወያየት በሰላማዊ መንገድ መሆን ይገባዋል ብለዋል።  ከሶማሊያም ሆነ ከጎረቤቶቿ ጋር በሰላማዊ መንገድ በመመካከር ለማግኘት መጣር እንደሚጠበቅባት አመላክተዋል።

የሶማሊላንድ ጉዳይም ቢሆን መፈታት ያለበት በሶማሊያ እና በሶማሊላንድ ህዝብ በኩል ነው ያሉት ምክትል ጸሃፊዋ በውጭ ሀይሎች ጣልቃ ገብነት ሊሆን አይገባም ብለዋል።

የአሜሪካ የአፍሪካ ጉዳዮች ምክትል ጸሐፊ ሞሊ ፊ በኦንላይን በነበራቸው ጋዜጣዊ መግለጫ በአዲስ አበባ ቆይታቸው ከበርካታ የኢትዮጵያ መንግስት ባለስለጣናት ጋር በተለያዩ ጉዳዮች መምከራቸውንም ጠቁመዋል።

ከኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ጋር ለሚደረግ ውይይትን ለማመቻቸት ሀገራቸው ዝግጁ መሆኗን የጠቆሙት በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ የተገኙት ማይክ ሀመር በመንግስት እና የአማራ ክልል ታጣቂ ሀይሎች ፋኖ ጋር ሰለማዊ መፍትሔ ለማፈላለግ ያለም ውይይት የሚደረግ ከሆነ ለመሳተፍ ዝግጁ ነን ሲሉ ገልጸዋል።  

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

ለፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት ትግበራን ለማገዝ አሜሪካ አሁንም ቁርጠኛ ናት ሲሉ የተደመጡት ሀመር ከፕሪቶርያው ስምምነት መካከል አንዲ የሆነውን ዲዲአርን ለማገዝ የሚውል ሀገራቸው 15 ሚሊየን ዶላር ለመለገስ መወሰኗን ገልጸዋል።

ከፕሪቶርያው ስምምነት በኋላ በክልሉ የሚፈጸሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች መቀነሳቸውን የጠቆሙት ሀመር ነገር ግን አሁንም በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ የኤርትራ ጦር መኖሩ እጅግ ያሳስበናል ብለዋል። በክልሉ ከቀያቸው ተፈናቅለው እና በአስከፊ ሁኔታ ላይ የሚገኙ ስደተኞች ወደ ቤታቸው መመለስ አለባቸው ሲሉ ገልጸዋል።

15 ወራትን ያስቆጠረውን የፕሪቶርያ የሰላም ስምምነት ለመተግበር የፌደራል መንግስቱ እና የትግራይ ግዜያዊ አስተዳደር ያሳዩትን ቁርጠኝነት የሚበረታታ ነው ብለዋል። አስ   

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button