ዜናቢዝነስ

ዜና፡ ከሁለት የዳታ ማይኒንግ ድርጅቶች የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ከሁለት ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ ማግኘቱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 13/2016 ዓ.ም፡- ሃያ አምስት የዳታ ማይኒንግ ድርጅቶች ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ጋር ለመሥራት ጥያቄ ማቅረባቸውንና ከእነዚህ ውስጥ አራቱ ሥራ መጀመራቸውን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ።

የዳታ ማይኒንግ ኩባንያዎቹ በሀገር ውስጥ ኃይል የሚጠቀሙ ቢሆንም የፍጆታ ሂሳባቸውን በዶላር እንዲከፍሉ ከስምምነት መደረሱን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

የኢንቨስትመንት ፍቃድና ሌሎች አስፈላጊ መስፈርቶችን ካሟሉት ከሃያ አምስቱ ድርጅቶች መካከል አራቱ ከ10 እስከ 100 ሜጋ ዋት ድረስ ኃይል መጠቀም መጀመራቸውን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የገበያና ቢዝነስ ልማት መምሪያ አቶ ህይወት እሸቱ መናገራቸውን መረጃው አመላክቷል።

ለመጀመሪያ ጊዜ በሀገር ውስጥ በውጭ ምንዛሪ ከተከናወነው ሽያጭ አስቀድመው ሥራ ከጀመሩት ከሁለቱ የዳታ ማይኒንግ ድርጅቶች ብቻ ከሁለት ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን ገልፀዋል።

የቀሪዎቹ ሁለት ድርጅቶች የፍጆታ ሂሳብ በቀጣዩ ወር መሰብሰብ እንደሚጀምር ተጠቁሟል።

በዳታ ማይኒንግ ዘርፍ ለመሰማራት ፍቃድ ከወሰዱትና ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ጋር የኃይል ሽያጭ ስምምነት ከተፈራረሙት አስራ ስምንት ድርጅቶች መካከል አምስቱ ግንባታ ሲጀምሩ አስሩ ደግሞ ግንባታ ለመጀመር በሂደት ላይ መሆናቸውን አቶ ህይወት ገልጸዋል ብሏል።

ሦስቱ የዳታ ማይኒንግ ድርጅቶች ግን ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ ባለመጀመራቸው በፍጥነት ወደ ሥራ እንዲገቡ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል ብለዋል፡፡

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

መስፈርቶቹን ካሟሉት የዳታ ማይኒንግ ድርጅቶች መካከል ሌሎች ሶስት ድርጅቶች ከተቋሙ ጋር የኃይል ሽያጭ ስምምነት ለመፈራረም በሂደት ላይ መሆናቸው ታውቋል፡፡

ከዚህ በኋላ የሚቀርብ የዳታ ማይኒንግ ድርጅቶች የኃይል ፍላጎት ጥያቄ የሚስተናገደው አስቀድመው የኃይል ፍላጎት ያቀረቡትን ድርጅቶች ጥያቄ ምላሽ ካገኘ በኋላ የሚኖረውን የኃይል አቅርቦት በመመርመር እንደሚሆን አቶ ህይወት መናገራቸውን መረጃው ጠቁሟል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button