ዜናህግ እና ፍትህ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና፡ “በትግራይ ክልል የዘር ማጥፋት ወንጀል እንደተፈጸ የሚያሳዩ ጠንካራ ማስረጃዎች አሉ”፡ ሪፖርት

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 28/ 2016 ዓ/ም፦ ተቀማጭነቱን በ #አሜሪካ ያደረገ ኒው ላይንስ ኢንስቲትዩት የተባለ ተቋም፣ “የኢትዮጵያ ኃይሎች በትግራይ ጦርነት ወቅት በክልሉ የዘር ማጥፋት ወንጀል መፈጸማቸውን” የሚያመላክት ጠንካራ ማስረጃዎች ማግኘቱን አዲስ ባወጣው ሪፖርት አስታወቀ። 

ተቋሙ ማክሰኞ ዕለት ባወጣው ባለ 120 ገጸ ሪፖርት፤ የመንግሥት ኃይሎች ከአጋር ኃይሎቻቸው ጋር በመሆን “የዘር ማጥፋት ተግባር ላይ መሳተፋቸውን” የሚያሳይ ማስረጃዎች መኖራቸውን ገልጿል።  በጦርነቱ ወቅት የጦር ወንጀሎች ወይም በሰበዓዊነት ላይ የሚፈጸም ወንጀል መፈጸሙን የሚያመላክቱ አሳማኝ ምክንያቶች መኖራቸውንም አክሎ ገልጿል። 

የኢትዮጵያ መንግሥት በአለም አቀፍ የፍትህ ፍርድ ቤት (ICJ) ክስ እንዲመሠረትበት ኒው ላይንስ ኢንስቲትዩት በሪፖርቱ ጠይቋል። 

ሪፖርቱ እንዳመላከተው የ #ኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት፣ የ #ኤርትራ መከላከያ ኃይል እና የአማራ ክልል ሚሊሻዎች በትግራይ ተወላጆች ላይ “የጅምላ ግድያ በመፈጸም እና በረሃብ  ዘር ማጥፋት አላማቸው ነበር”።

አራት የዘር ማጥፋት ወንጀል ድርጊቶችን ማለትም፤ የትግራይ ተወላጆችን መግደል፣ ከባድ ጉዳት ማድረስ፣ ለሕይወት አስጊ ሁኔታ መፍጠር እና በትግራይ ተወላጆች መካከል መዋለድን መከላከል መፈጸሙን ሪፖርቱ አክሎ አስታወቋል።

የኒው ላይንስ ኢንስቲትዩት ሪፖርት መስከረም ወር ላይ ይፋ ከሆነው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሪፖርት ጋር የሚስማማ ሲሆን፤ ሪፖርቱ የተጠቀሱት አካላት “የጦር ወንጀል ፈጸመዋል” ሲል ከሷል። ሪፖርቱ አለም አቀፉ ማህበረሰብ በኢትዮጵያ ላይ በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ጫና እንዲያሳድር እና በአለም አቀፉ የፍትህ ፍርድ ቤት ህጋዊ እርምጃ እንዲወስድ ጥሪ አቅርቧል። አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button