ዜናፖለቲካ

ዜና፡ በአማራ ክልል ለምርት ዘመኑ የሚያስፈልግ ማዳበሪያ በእጀባ እየተጓጓዘ በመሆኑ መዘግየት መኖሩን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 22/2016 ዓ.ም፡- የአማራ ክልል መንግስት 8 ነጥብ 05 ሚሊየን ኩንታል ማዳበሪያ ግዥ መፈጸሙን እና 2 ነጥብ 6 ሚሊየኑ ከወደብ ወደ ክልሉ መግባቱን የክልሉ ግብርና ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር ድረስ ሳህሉ አስታወቁ።  

ቀሪውን ማዳበሪያ በፍጥነት ለማጓጓዝም ሰላም አስፈላጊ መኾኑን የጠቀሱት ዶ/ር ድረስ የማዳበሪያ ዝርፊያን ለመከላከል በእጀባ ስለሚጓጓዝ መዘግየት መኖሩን ጠቁመው ስለዚህ ”ማዳበሪያ እንዳይዘገይ ሕዝቡ ለሰላሙ ከመንግሥት ጎን መቆም አለበት” ማለታቸውን አሚኮ ዘግቧል።

በክልሉ የተከሰሠተው የሰላም እጦት በግብርናው ዘርፍ ላይ ተጽዕኖ አሣድሯል፤ ጉዳትም አስከትሏል ያሉት ሃላፊው ከሰሜኑ ጦርነት ጀምሮ እስካሁን ያለው የሰላም እጦት ንብረት እያወደመ መኾኑን እና እንደልብ ተንቀሳቅሶ ለመሥራት ማስቸገሩን እንደ ፈታኝ ሁኔታ ማንሳታቸውን አመላክቷል።

የሰላም እጦቱ በተለይም በመስኖ እና በተፈጥሮ ሃብት ልማት ጥበቃ ሥራዎች ላይ ውስንነቶችን መፍጠሩንም ጠቁመዋል። ከባለሙያዎች ጋር የስልክ ግንኙነት በማድረግ ለመምራት እና ለማገዝ ጥረት እየተደረገ መኾኑንም ነው ኀላፊው ያነሱት።

ሌሎች የግብርና ሥራዎችንም ለማከናወን ሰላም አስፈላጊ ስለኾነ ሕዝቡ ለሰላም ቁርጠኛ ኾኖ እንዲቆም አሳስበዋል።ግብርናውን ለማዘመን እየተሠራ መኾኑንም ኀላፊው ገልጸዋል።

ጥራት ያለው ምርት ለማግኘት ትኩረት መሰጠቱን የገለጹት ዶ/ር ድረስ ሳህሉ የግብርና ጥራት ቁጥጥር ባለሥልጣን መቋቋሙንም ጠቁመዋል።

በተመሳሳይ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ታጣቂ ሀይሎች ወደ ክልሉ የሚጓጓዝ ማዳበሪያ ላይ ልዩ ጥበቃ እናደርጋለን የሚል መልዕክት ያዘሉ ንግግሮችን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዳያ ዘዴዎች እያሰራጩ ይገኛሉ። በአማራ ክልል ከመንግስት የጸጥታ ሀይሎች በትጥቅ የታገዘ ትግል በማካሄድ ላይ የሚገኙ ቡድኖች በክልሉ ማዳበሪያ ጭነው የሚንቀሳቀሱ መኪኖች ምንም አይነት እንግልት እንዳይደርስባቸው የሚያሰስቡ ሀሳቦች በመልዕክቶቻቸው በማሰራጨት ላይ ይገኛሉ። አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button