ዜናፖለቲካህግ እና ፍትህ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና፡ ከደቡብ አፍሪካ መንግስት ጋር በወንጀል የሚፈለጉ ሰዎችን አሳልፎ የመስጠት ስምምነት መፈረሙን የፍትህ ሚኒስትሩ አስታወቁ

አዲስ አበባ፣ ጥር 23/2016 ዓ.ም፡- በሕግና ፍትሕ ጉዳዮች ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማሳደግ በተሰራው ስራ ከደቡብ አፍሪካ መንግስት ጋር በወንጀል የሚፈለጉ ሰዎችን አሳልፎ የመስጠት ስምምነት መፈረሙን የፍትሕ ሚንስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 13ኛ መደበኛ ጉባዔ ላይ ተገኝተው ባቀረቡት የግማሽ ዓመት ሪፖርት ላይ አስታውቀዋል።

በተጫሪም ከደቡብ ሱዳን፣ ከቦትስዋና እና ከቻይና መንግስት ጋር በአሳልፎ መስጠትና በወንጀል ጉዳዮች የጋራ የህግ ትብብር የሁለትዮሽ ስምምነቶችን ለማድረግ ረቂቅ ስምምነቶች ተዘጋጅተው ለሚመለከታቸውና ለባለድርሻ አካላት ተደራሽ መደረጋቸውን ሚንስትሩ በሪፖርታቸው አመላክተዋል፡፡

በአማራ ክልል ከአስቸኳይ ግዜ አዋጁ ጋር በተያያዘ ታስረው በሚገኙ ከሰባት መቶ በላይ የሚሆኑ ተጠርጣሪዎች የሰብዓዊ መብት አያያዝ ሁኔታ ተመርምሮ ለአስቸኳይ ጊዜ አስፈጻሚ እዝ መቅረቡን የፍትህ ሚኒስቴሩ ዶ/ር ጌዴዮን ጢሞቴዎስ አስታወቁ።

የሰብዓዊ መብት አያያዝ ሁኔታቸው ተመርምሮ ለአስቸኳይ ጊዜ አስፈጻሚ እዝ የቀረቡት በባህር ዳር፣ በጎንደር እና በኮምቦልቻ ከተሞች በሚገኙ የማቆያ ስፍራዎች የሚገኙ 706 ተጠርጣሪዎች መሆናቸው የፍትህ ሚኒስትር ጌዴዮን ጤሞቲዎስ (ዶ/ር) የሚኒስቴሩን የስድስት ወራት አፈጻጸም ሪፖርት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡበት ወቅት ገልጸዋል።

ሚንስትሩ ለ58 ሺህ 4 መቶ 78 በማረሚያ ቤትና በፖሊስ ማረፊያ ቤት በሕግ ቁጥጥር ስር የዋሉ ታራሚዎችን በመጎብኘት በተገኙ ግኝቶች ላይ የእርምት እርምጃ መወሰዱን ገልጸዋል፡፡

ከ13 ሺ 4 መቶ 70 የክስ መዛግብት ውስጥ ለ3ሺ 503 መዛግብት ውሳኔ መሰጠቱን የፍትሕ ሚንስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ጌዲዮን ባቀረቡት የግማሽ ዓመት ሪፖርት ላይ ጠቅሰዋል፡፡ አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button