ዜናፖለቲካ

ዜና፡ በአዲስ አበባ በቀጣይ እሁድ የተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ እንዳይካሄድ መንግስት ጫና እየፈጠረ ነው ሲሉ አስተባባሪዎቹ ተናገሩ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 27/2016 ዓ.ም፡- በአዲስ አበባ በቀጣይ እሁድ ጦርነት ይቁም ሰላም ይሰፈን በሚል መሪ ሃሳብ ለማካሄድ የጠራነውን ሰላማዊ ሰልፍ እንዳናካሂድ መንግስት ጫና እየፈጠረብን ነው ሲሉ አስተባባሪዎቹ ገለጹ። አስተባባሪዎቹ ሰልፉ የተጠራውም በፖለቲከኞች፣ ሲቪል ተቋማት እና በጎ ፈቃደኛ ግለሰቦች ነው ማለታቸውን የጀርመን ድምጽ በዘገባው አስታውቋል።

ሰላማዊ ሰልፉን እሑድ ኅዳር 30 ቀን 2016 ከአራት ሰዓት እስከ ስምንት ሰዓት እንዲካሄድ ብለን ነው የጠራነው፤ ዋና መልእክቱም ጦርነት ይቁም ሰላም ይስፈን ሚል ነው፤ ሀሳቡን ለሚደግፍ ማንኛውም ሰው ነው ጥሪው የቀረበው ሲሉ ከሰልፉ አስተባባሪዎች አንዱ ፖለቲከኛ የሺዋስ አሰፋ መናገራቸውን ዘገባው አስደምጧል።

የመንግስት አካላት ሰልፉ እንዳይደረግ የተለመደው ማስፈራሪያ እየተደረገብን ነው ሲል ሰልፉን የሚያስተባብረው አዘጋጅ ኮሚቴ ሰኞ ህዳር 24 ቀን 2016 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ አስታውቋል ያለው ዘገባው ሰልፉን የጠራው አስተባባሪ ኮሚቴው በሰኞው መግለጫው የፌዴራል ፖሊስ፣ አዲስ አበባ ፖሊስ እንዲሁም የከተማዋ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ከህገመንግስት መርህ ውጪ ዛቻ ሰንዝሮብኛል ማለታቸውን አስደምጧል።

ኮሚቴው ሰላማዊ ሰልፉን የማካሄድ ሂደቱ በህግ አግባብ ስርዓትን የተከተለ ነው ማለቱንም አካቷል።ስለዚሁ መግለጫ የተጠየቁት አቶ የሺዋስ አሰፋ፤ “ጦርነት ይቁም የሚል ሀሳብ መደገፍና መበረታታት የነበረበት ነው፤ እኛ የሀገሪቱን ህግ መሰረት አድርገን ኩለት ቀን በፊት የሚለውንም ከ12 ቀን በፊት ሰልፉን ማድረግ እንደምንፈልግ አሳውቀናል፤ ይሁንና ከንቲባ ጽ/ቤት ለዚህ መልስ አልሰጠንም፤ ከአዲስ አበባ እና ፌዴራል የፖሊስ አመራሮች አነጋግረውን ነበር፤ ሊያነጋግሩን ጥሪ ስያቀርቡልንም ቦታውና ቀኑን በተመለከተ የሚያወያዩን መስሎን ነበር፤ ይሁንና የተለመደውን ችግር ይፈጠራል ችግር ከተፈጠረ እርምጃ እንወስዳለን የሚል ማስፈራሪያ ውስጥ ገቡ በሉ ደህና እደሩ ብለን ወጣን” ማለታቸውን አስደምጧል፡፡

በአዲስ አበባ በቀጣይ እሁድ ህዳር 30 ቀን 2016 ዓ.ም ሊካሄድ የታሰበውን ሰልፍ መንግስት መከልከሉን አፍሪካን ፕሬስ ኤጀንሲ በዘገባው አስታውቋል። ከሰልፉ ጋር በተያያዘ በርካታ የከተማዋ ወጣቶች ታፍሰው እየታሰሩ ነው ብሏል። ከጅምላ እስሩ በተጨማሪ የከተማዋ የጸጥታ ሀይሎች የቤት ለቤት አሰሳ እያካሄዱ መሆኑን አመላክቷል። መንግስት ሰልፉ እንዳናካሂድ ክልከላ ቢፈጽምም ማካሄዳችን የማይቀር ነው ሲሉ አስተባባሪዎቹ መግለጻቸውን አስታውቋል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button