ዜናፖለቲካህግ እና ፍትህ

ዜና፡ በኢትዮጵያ በሰብዓዊ መብት ጥሰቶች የተሳተፉ ሊከሰሱ እንደሚገባ የሽግግር ፍትሕ ባለሙያዎች ቡድን ምክረሃሳብ ማቅረቡ ተጠቆመ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 22/2016 .ም፡ በሰብዓዊ መብት ጥሰቶች የተሣተፉ ሊከሰሱ እንደሚገባ በኢትዮጵያ ሊተገበር ለታቀደው የሽግግር ፍትኅ እስከ ፖሊሲ ዝግጅት ያሉ ተግባራትን የማከናወን ኃላፊነት ተሰጥቶት ኅዳር 2015 ዓ.ም. የተቋቋመው 13 አባላት ያሉት የባለሙያዎች ቡድን ባወጣው ሪፖርት መግለጹ ተጠቆመ።

ቡድኑ በሁሉም ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች አከናንኳቸው ባላቸው 58 ህዝባዊና ሌሎች 22 መድረኮች የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች ተጎጂዎች ላይ አተኩሮ ሁሉንም የማኅበረሰብ ክፍሎች ያካተተ የግብዓት ማሰባሰቢያ ምክክር መደረጉን ቪኦኤ በዘገባው አስደምጧል።

በስምንት የፖሊሲ አማራጮች ላይ በተደረገው ምክክር አብዛኞቹ ተሳታፊዎች የደገፏቸውና አቋም የወሰዱባቸው ዋና ዋና ግኝቶችንና ምክረሃሳቦቹንም ይፋ ያደረገ ሲሆን፣ ከነዚህም መካከል የወንጀል ተጠያቂነት ጉዳይ እንደሚገኝበት አመልክቷል።

ጉልህ በሆኑ ጥሰቶች ላይ ያተኮረ የክሥ ሂደት ሊኖር እንደሚገባ ግብዓቶቹን መነሻ አድርጎ የገለፀው የባለሙያዎቹ ቡድን ከፍተኛ ተሳትፎ እንደነበራቸው በሚረጋገጥ ሰዎች ላይ ክሥ ሊመሥረት እንደሚገባ እንደሚያሳስብ የባለሙያዎች ቡድኑ አባል ቃል ኪዳን ደረጀ መናገራቸውን አስደምጧል።

ክሱ በአዲስ ዐቃቤ ሕግ ተቋም መመራትና አዲስ በሚቋቋም ልዩ ፍርድ ቤት መታየት እንዳለበትም መምከራቸውን ጠቁሟል።

እውነት የማፈላለግ እና የዕርቅ ተግባራትም አዲስ በሚቋቋም ገለልተኛና ተቀባይነት ያለው የሃቅ አፈላላጊ ኮሚሽን አማካኝነት ሊከናወኑ እንደሚገባ ተገልጿል ያለው ዘገባው ኮሚሽኑ ሲቋቋም የውጭ ባለሙያዎችን ማካተት እንደሚኖርበት አስቀምጧል።

የሽግግር ፍትሕ ሂደቱ ከየትኛው ጊዜ ይጀምር በሚል ከቀረቡ አምስት አማራጮች ውስጥ “ለክሥ ጉዳይ ከ1987 ዓ.ም. ጀምሮ ለእውነት ማፈላለግ፣ እርቅ ማስፈንና ማካካሻ ጉዳይ ግን መረጃና ማስረጃ እስከተገኘበት ጊዜ ድረስ” የሚለው አማራጭ ተቀባይነት ማግኘቱ ተብራርቷል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

በተመሳሳይ የጅምላ ግድያ በተፈጸመባቸው ቦታዎች ሐውልት፣ ማስታወሻ ወይም ሙዚየም በማቆምና የገንዘብ ካሳን በሚያካትት አግባብ ሊከናወን እንደሚገባ ከተሳታፊዎች ሐሳብ መቅረቡን ቡድኑ ማስታወቁን ሪፖርተር በዘገባው አስታውቋል።

የማካካሻ ሥርዓቱ አዲስ በማቋቋም ኮሚሽን አማካይነት ሊመራ እንደሚገባ አብዛኞቹ ተሳታፊዎች የገለጹ መሆናቸውን፣ የሽግግር ፍትሕ የጊዜ ማዕቀፍ የት ይጀመር ለሚለው ለክስ ጉዳይ ከ1987 ጀምሮ ለእውነት ማፈላለግ፣ ዕርቅ ማስፈንና ለማካካሻ ጉዳይ፣ ነገር ግን መረጃና ማስረጃ እስከተገኘበት ጊዜ ሊዘረጋ ይገባል የሚል ሐሳብ መነሳቱን የቡድኑ አባላት ሪፖርት ማመላከቱን ዘገባው አካቷል።

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button