ዜናፖለቲካ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና፡ ኢትዮጵያ በ2024 ግጭት ሊያስተናግዱ ከሚችሉ አስር ሀገራት አንዷ መሆኗን ክራይስስ ግሩፕ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 22/2016 .ም፡ ኢትዮጵያ በአዲሱ የፈረንጆቹ አመት በ2024 ግጭት ሊከሰትባቸው ከሚችሉ አስር ሀገራት አንዷ መሆኗን ክራይስስ ግሩፕ ባስነበበው ሪፖርት አስታወቀ።

ከቅርብ ግዜያት ወዲህ አለማችን በጦርነት እየተናጠች እንደሚገኝ የጠቆመው ቡድኑ ከ2004 ዓ.ም ወዲህ በከፍተኛ ሁኔታ ወደ ጦርነት የሚገቡ ሀገራት እየጨመረ መምጣቱን አስታውቋል። ባለፉት ሶስት አመታት የትግራዩን ጦርነት ጨምሮ በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል እንዲሁን የአዘርባጃን እና አርመንያ ጦርነት አውዳሚ አንደነበር ጠቅሷል።

ጦርነቶቹን ለማርገብ በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ውይይቶች ለማካሄድ ጥረት መደረጉን የጠቆመው ቡድኑ ወደ ፖለቲካ ውይይት አለማደጋቸውን ተችቷል።

በኢትዮጵያ በትግራይ የተካሄደውን ጦርነት ለማስቆም የሰላም ድርድር ቢካሄድም የጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድን ስልጣን ከማደላደል ያለፈ የቀጠናውን የወደፊት ሰላም ታሳቢ ያደረገ ውጤት አላመጣም ሲል ገልጿል።

የትግራይ ጦርነት በፕሪቶርያው ስምምነት መፈረም መቆሙን ተከትሎ ኢትዮጵያ ያሳለፍነውን የፈረንጆቹን አመት 2023ን በመልካም ዜና መጀመሯን ያወሳው ክራይስስ ግሩፕ ስምምነቱ በትግራይ ጦርነት ቢያስቆምም በሌላኛው የሀገሪቱ ክፍል ሌላ ጦርነት እንዲጀመር ምክንያት መሆኑን አስታውቋል።

በ2015 ዓ.ም ነሃሴ ወር ላይ በአማራ ክልል ተፈጥሮ በነበረው ግጭት የፋኖ ታጣቂዎች በርካታ ከተሞችን ተቆጣጥረው እንደነበር ያወሳው ቡድኑ በመንግስት ሀይሎች ከከተሞች ቢወጡም አሁንም በርካታ የክልሉ ቦታዎች በመንግስት ቁጥጥር ስር አይደሉም፣ ክልሉን የሚያስተዳድረው የአብይ ፓርቲ በክልሉ ተቀባይነት አጥቷል ብሏል።

ለጠ/ሚኒስትር አብይ አገዛዝ አማራ ክልል ብቻ አይደለም ራስምታት የሆነበት ሲል የገለጸው ክራይስስ ግሩፕ በኦሮምያም ከፍተኛ ትግል እንደገጠመው አመላክቷል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

በሀገሪቱ ታላላቅ ሶስት ክልሎች ኦሮምያ፣ አማራ እና ትግራይ የተፈጠረው ቀውስ ለማዕከላዊ መንግስቱ ትልቅ ስጋት መሆኑን ጠቁሟል።

ጠ/ሚኒስትር አብይ ከትግራይ ጋር የተደረሰውን የሰላም ስምምነት በማስጠበቅ በኦሮምያ እና አማራ ክልሎች ያሉትን ጦርነቶች ማስቆም ብቻ ሳይሆን በሀገሪቱ ብሔሮች ላይም መስማማትን መፍጠር እንደሚጠበቅባቸው አሳስቧል። የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ጭንቅ ላይ ነው ሲል ገልጿል።

የጠ/ሚኒስትር አብይ እና የፕሬዝዳንት ኢሳያስ ግንኙነት መሻከር ትልቅ ስጋት መሆኑን ጠቁሟል። ሁለቱም በድንበር አከባቢ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰራዊት ማንቀሳቀሳቸው በማንኛውም ሰአት ግጭት ሊጫር እንደሚችል ስጋት ይፈጥራል ብሏል።

እነዚህን ነጥቦች ያስቀመጠው ክራይስስ ግሩፕ በ2024 ግጭት ሊከሰትባቸው ከሚችሉ አስር ሀገራት አንዷ መሆኗን አስታውቋል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button