ዜናቢዝነስ

ዜና፡ ለሱዳን የሚቀርበው የኤሌክትሪክ ሀይል መጠን 50 በመቶ እንዲቀንስ ተደረገ፣ 70 ሚሊየን ዶላር እዳ አለባት ተብሏል

አዲስ አበባ፣ ጥር 29/2016 ዓ.ም፡- ኢትዮጵያ ከውጭ ሀገር የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ያገኘችው ገቢ ከ47 ሚሊዮን 514ሺ ዶላር ብቻ መሆኑን አስታወቀች።

በግማሽ አመቱም ከውጭ የኤሌክትሪክ ሽያጭ 66 ሚሊዮን 274 ሺ 260 ዶላር ለማግኘት ታቅዶ 47 ሚሊዮን 514 ሺ 16 ዶላር ለማግኘት መቻሉንና ይህም አፈጻጸሙ 72 በመቶ መሆኑን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሽያጭና ገቢዎች አስተዳደር ኃላፊ ሚኒሊክ ጌታሁን መናገራቸውን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘግቧል።

ለጎረቤት ሀገራት ከሚቀርብ ከኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ አፈጻጸም ተቋሙ ባቀደው ልክ ላለመሳካቱ የተለያዩ ምክንያቶች መኖራቸውን የገለጹት ኃላፊው የኤሌክትሪክ ኃይል ከሚላክላቸው ጎረቤት ሀገር መካከል አንዷ የሆነችው ሱዳን ባለባት የጸጥታ ችግር ሳቢያ የተላለፈላትን ኃይል ክፍያ በአግባቡና በወቅቱ እየከፈለች አለመሆኑ አንዱ ምክንያት መሆኑን እንደገለጹለት ዘገባው አስታውቋል።

በመንግሥት ደረጃ ውሳኔ እስከሚሰጥበት ድረስ ለሱዳን የሚቀርበው የሀይል መጠን 50 በመቶ እንዲቀነስ መደረጉን ሀላፊው ጠቁመዋል ያለው ዘገባው ኢትዮጵያ የምታገኘውም ገቢ ላይ ግን አሉታዊ ሚና መጫወቱን አመላክቷል።

አቶ ሚኒሊክ በዘንድሮው በጀት አመት ለሱዳን ከቀረበ የኤሌክትሪክ ኃይል ምንም ዓይነት ገቢ አለመሰብሰቡና በጥቅሉም የ 70 ሚሊዮን ዶላር ዕዳ እንዳለባት መግለጻቸውን ዘገባው አስታውቋል።

ጅቡቲንና ኬንያን በሚመለከትም ይወስዳሉ ተብሎ ከታሰበው የኃይል መጠን ፍላጎታቸው የቀነሰ መሆኑን ሃላፊው መግለጻቸውን ያካተተው ዘገባው ይህም በተወሰነ ተጽእኖ ማሳደሩና የግማሽ አመቱ ክንውን ዝቅ እንዲል ማድረጉን አስታውቀዋል ብሏል።

ኃላፊው እነዚህ ችግሮች ቢኖሩም የውጭ የኃይል አቅርቦት ላይ ከአምናው ተመሳሳይ ወር ጋር ሲወዳደር 15 በመቶ ከፍ ብሏል ማለታቸውንም ዘገባው አካቷል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

አቶ ሚኒሊክ በዘንድሮው ግማሽ አመት ተቋሙ ለውጭና ለሀገር ውስጥ 8 ሚሊዮን 505 ሺ 725 ነጥብ 416 ሜጋዋት ኃይል መጠን ለመሸጥ ታቅዶ 8 ሚሊዮን ሜጋ ዋት ኃይል መጠን መሸጥ መቻሉን አብራርተዋል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button